በመዲናችን አዲስ አበባ በዚህ ሚያዝያ ወር ሶስ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በመዲናችን አዲስ አበባ በዚህ ሚያዝያ ወር ሶስት ዓለም አቀፍ ስፖርታዊ ኩነቶች ይከናወናሉ።

በዚህ ወር ከሚካሄዱ ሶስት ዓለምአቀፍ ስፖርታዊ ኩነቶች ውስጥ አንዱ በመጪው ቅዳሜ የሚካሄደው የአዲስ አበባ ግራንድ ፕሪ የአንድ ቀን የአትሌቲክስ ውድድር ነው።

ይህ ውድድር በመዲናችን አዲስ አበባ ሲካሄድ የመጀመሪያው ሲሆን  ለዘርፍ  መንግስት በሰጠው ትኩረት የስፖርት መሰረተ ልማቶች መስፋፋት እንደ ምክንያት ሊገለጽ ይችላል።

ውድድሩ ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ እና ብዙ ተከታይ ያላቸው አትሌቶች ይሳተፉበታል። የአዲስ አበባ ግራንድ ፕሪ ሚያዝያ 10  በአዲስ አበባ ስታዲዮም የሚካሄድ ይሆናል። 

በዚሁ ሚያዝያ ወር ከሚካሄዱ ውድድሮች ውስጥ ሲቲ ማውንቴን ባይክ ኢሊሚኔተር ዓለም አቀፍ የብስክሌት ውድድር እና ግራንድ ኢትዮጵያን ረን የሚካሄዱ ይሆናል።

 ከተማ አስተዳደሩ ውድድሩን ለማሳካት ከባለድርሻ አካላት ጋር  በቂ ዝግጅቶች ከማድረግ በዘለለ በኢትዮጵያ ያሉትን የስፖርት መሰረተ ልማቶች ለማስተዋወቅ የሚያስችሉ ሥራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.