መዲናችን ለስፖርት ዘርፉ በሰጠችዉ ልዩ ትኩረት...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

መዲናችን ለስፖርት ዘርፉ በሰጠችዉ ልዩ ትኩረት እና ባስመዘገበቻቸዉ የልማት ስኬቶች በዓለም አቀፍ የስፖርት መድረክ ተመራጭ እንድትሆን አስችሏታል፡፡

ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ በመዲናችን አዲስ አበባ የስፖርቱን ዘርፍ ለማዘመንና ተደራሽነቱን ለማስፋፋት በርካታ ውጤታማ ተግባራት በመከናወናቸዉ የከተማዋን የስፖርት ገጽታ ከመቀየር፤ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስሮችን ከማጠናከር ባሻገር በዓለም አቀፍ የስፖርት መድረክ ተመራጭ እንድትሆን አስችለዋታል፡፡

ከ1,589 በላይ ደረጃቸዉን የጠበቁ ዘመናዊ እና ምቹ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች በከተማዋ የተገነቡ ሲሆን ተተኪ ስፖርተኞችን ከማፍራት አኳያም በከተማዋ በሚገኙ 11ዱም ክፍለ ከተሞች 723 የታዳጊ ወጣቶች የስፖርት ስልጠና ጣቢያዎችን ተመርቀዉ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡

በመዲናዋ ያሉ የስፖርት መሰረተ ልማቶች በተለያዩ የእድሜ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ታዳጊ ህፃናት እና ወጣቶች፤ለባለሙያዎች እና ለስፖርተኞች እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚዘጋጁ ስፖርታዊ ዉድድሮች ጭምር ታሳቢ ተደርገዉ የለሙ የእግር ኳስ፤የእጅ ኳስ፤የቅርጫት ኳስ፤የሜዳ ቴኒስ፤የመዋኛ ገንዳ፤የቤት ውስጥና የውጪ ጂም፣ የዌልነስ ሴንተር እና የአጭር እርቀት የመሮጫ ትራኮች ዘመናዊና ባህላዊ የመጫወቻ ስፍራዎች እና የአሸዋ ላይ ስፖርት ሜዳዎች የተካተተባቸዉ የዘርፉ የስኬት ማሳያዎች ናቸዉ፡፡

ትዉልድ በአካልና በአዕምሮ እንዲታነፅ ታሳቢ ተደርገው የተገነቡ የስፖርት ማዘዉተሪያዎች በስፖርት ማዘዉተሪያ ቦታዎች እጥረት ምክንያት ወጣቶች በመኪና መንገዶች ላይ በመጫወት የሚደርስባቸዉን አደጋ በመቀነስ፤ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስርን በማጠናከር፤ለከተማዋም ሆነ ለሀገር የሚተርፉ የስፖርት ተሰጥኦ ያላቸው ወጣቶችን በየደረጃው እንዲወጡ በማስቻል ጤናማና አምራች ዜጋን ለመፍጠር የተያዘው ግብ ተጨባጭ ውጤቶች እንዲመዘገቡ አስችሏል፡፡

በመሆኑም ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በመዲናችን አዲስ አበባ ሶስት ዓለም አቀፍ ሲቲ ማውንቴን ባይክ ኢሊሚኔተር ዓለም አቀፍ የብስክሌት ውድድር፣ ግራንድ ኢትዮጵያን ረን እና የአትሌቲክስ ውድድሮችን ለማዘጋጀት ተመራጭ እንድትሆን አስችሏታል፡፡

ይህ የተቀናጀ የልማት ዘርፍ ከተማ አስተዳደሩ በዓለም አቀፍ ግንኙነት፤በስፖርት ዲፕሎማሲ እና በስፖርት መሰረተ-ልማት መስፋፋት ላከናወናቸዉ ስኬቶች አንዱ ተጨባጭ እዉነታ ነዉ፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.