የጋራ ግብረ-ኃይሉ በዓሉ ያለምንም የፀጥታ ችግር...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የጋራ ግብረ-ኃይሉ በዓሉ ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲከበር ዝግጅት ማጠናቀቁን ገለጸ

የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ሕዝበ ክርስቲያኑ ትንሣኤን በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲያከብር በሁሉም ክልሎች እና በሁለቱም ከተማ አስተዳደሮች ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ተግባር መግባቱን አስታወቀ፡፡

ሕዝቡም ሰላምና ደኅንነትን ለማረጋገጥ በሚካሄደው የፀጥታ ማስከበር ሥራ ውስጥ በባለቤትነት እያደረገ ያለውን ተሳትፎ የበለጠ አጠናክሮ በመቀጠል የአካባቢውን ሰላምና ደኅንነት የሚያውኩ አጠራጣሪ ነገሮችን ሲመለከት ለፀጥታ አካላት ጥቆማ በመስጠትና አስፈላጊውን ትብብር በማድረግ ከጋራ ግብረ-ኃይሉ ጎን በመሆን የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪውን አቅርቧል።

ግብረ-ኃይሉ ለመላው የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞቱንም አስተላልፏል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.