የኮፕ32 አስተናጋጅ እንደሆነ ሀገር፤ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ኮሚቴ በይፋ በማቋቋም ዝግጅቷን ቀደም ብላ ጀምራለች።
ይህን ሂደት በግልጽ ግብ እና በላቀ ምልከታ ለመምራት ቁልፍ አመራር መድበናል። ይህን ተከትሎ የኮፕ ፕሬዝደንት መዋቅር የተቀናጀና የላቀ ውጤት የሚያስገኙ የቅድሚያ ተግባራቱን ጀምሯል።
ዛሬ ከብሔራዊ ኮሚቴው ጋር በነበረን ስብሰባ፤ በተለያዩ ዘርፎች የተከናወኑ የእስካሁን ሥራዎችን በመገምገም ክፍተቶችን የመለየት እና ሁሉም ጥረቶቻችን ከሀገራዊ ርዕያችን ጋር የተጣጣሙ መሆናቸው ተዳሷል። በመድረኩ ከግምገማ ባሻገር የጋራ ቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጠንበታል። ትኩረታችን ግልጽ ነው፤ በጠንካራ ትብብር፣ በተዋሃደ ታላቅ ርዕይ እና የጋራ ጽኑ ትጋት ተናበን ይህን ዓለም አቀፍ ሁነት በልህቀት በማስተናገድ የሀገርን ታላቅነት ዳግም ማሳየት ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.