የመራጮች ምዝገባ 5 ቀን ብቻ ቀረው!! እኔ በ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የመራጮች ምዝገባ 5 ቀን ብቻ ቀረው!! እኔ በጊዜ የምርጫ ካርዴን ወስጃለሁ፤ እናንተስ?

እንደ ሰለጠኑት ሀገራት በእኛም  ሀገር የመንግሥት ሥልጣን ከሕዝብ የሚመነጭና በሕዝብ የምርጫ ካርድ የሚወሰን መሆን አለበት፤ ይኖርበታልም።

ምርጫ በሁሉም አካባቢ ሰላማዊና የተረጋጋ ሁኔታ እንዲሰፍን፣ የዴሞክራሲ  እና የሰለጠነ የፓለቲካ ሥርዓትን ለመገንባት፣ የተጀመሩ ልማቶችን ለማስቀጠል፣ እንዲሁም ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ወሳኝ ነው። 
ከምርጫ ውጪ የሚደረግ ማንኛውም እንቅስቃሴ በአገር ላይ ከፍተኛ ጥፋት ያመጣል።
ስለሆነም፤ ሁላችሁም የምርጫ ካርዳችሁን ወስዳችሁ የመምረጥ መብታችሁን ተጠቀሙ። መብታችሁን ተጠቅማችሁ ባትመርጡ፣  ሌሎች ተመዝግበው   በመረጡት መንግሥት መተዳደራችሁ የማይቀር መሆኑን በመገንዘብ መብታችሁን ተጠቀሙ።

የምርጫ ካርድ ወስዶ መምረጥ ለሀብታሙም፣ ለደሃውም፣ ለተማረውም፣ ላልተማረውም፣ ዕድሜው ለመምረጥ ለደረሰ ወጣት፣ ለጎልማሳው፣ ለአዛውንቱ፣ ለሴቱም ሆነ ለወንዱ፣ ለባለስልጣንም፣ ለሌላውም ዜጋ እኩል የተሰጠ መብት ስለሆነ መብታችሁን ተጠቀሙበት!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.