በከተማችን አዲስ አበባ የገነባናቸው ዘመናዊ የስፖርት መሠረተ ልማቶች ውጤቱ አገራችን በአትሌቲክስ ዘርፍ ያላትን ታላቅ ዝና ዳግም ለማረገገጥ እድል ይሰጣል።
የተገነቡት የስፓርት መሰረተ ለማቶች ዓለም አቀፍ ስፖርታዊ ኩነቶች፣ ከተማችን ማንኛውንም ዓይነት ዓለም አቀፍ ውድድር የማስተናገድ ብቃትና ደረጃ ላይ መድረሷን የሚያሳዩ ናቸው።
በመዲናችን የሚከናወኑ ውድድሮች ተተኪ አትሌቶችን ከማነቃቃታቸውም በላይ ለስፖርታዊ ቱሪዝም ዕድገት የጎላ ፋይዳ አላቸው።
ከተማችን ለነዋሪዎቿ ምቹ ፤ሳቢ ከማድረግ ባለፈ፣ ለዓለም አቀፍ ኩነቶች የስበት ማዕከል እየሆነች መምጣቷን በተግባር ያሳየ እውነታ ነው።
አለም አቀፍ እና ሀጉር አቀፍ መድረኮች ማዘጋጀት ሀገራዊ አንድነትን በማጠናከር ረገድ ትልቅ ፋይዳ አለው።
አትሌቶቹም ሆነ እንግዶቹ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ስለ ኢትዮጵያ ታሪክና ውበት ይበልጥ እንደሚገነዘቡ ተስፋ አለኝ።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.