በእድገት ግስጋሴ ላይ ያለች ከተማ አዲስ አበባ

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በእድገት ግስጋሴ ላይ ያለች ከተማ አዲስ አበባ

የኢትዮጵያ መዲና የሆነችው ውቧ አዲስ አበባ ገፅታዋን እየለወጠች፣ ነዋሪዎቿን እያቀፈች፣ መስህቦቿን እያበዛች፣ ሩቅ እያለመች በፍጥነትም እየተራመደች ነው፡፡

በእርግጥም አዲስ አበባ በፍጥነት እየተለወጠች ነው፡፡ ቃል ገብታ፣ ጊዜ ቆርጣ የምትጀምራቸውን ፕሮጀክቶች በጊዜ በፍጥነትና በጥራት እያጠናቀቀች ሪቫን እየቆረጠች ነው፡፡ አዲስ አበባ የአፍሪካ ዓይን የሆነች ዓለም አቀፍ ከተማ ለመሆን የሚያስችላትን ጎዳና ይዛለች፡፡

ውብ የቱሪዝም መዳረሻ፣ ለዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ ኩነቶች የምትመረጥ፣ ንፁህ፣ አረንጓዴ ሥፍራዎች ነገ የተሻለች ከተማ እንደምትሆን ትልቅ ማሳያ በመሆን ሩቅ እያለመች፣ አሰራሯን እያዘመነች ህብረ ብሄራዊነቷን የጠበቀች ሰላም ያላት ውብ ከተማ አዲስ አበባ ።

በተለይ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሰው ተኮር ልማቷ የብዙ ነዋሪዎቿን እንባን ያበሰች፣ መደገፊያ መጠጊያ የሆነች፣ ተስፋን የሰጠች.....የተጣሉትን ያስታወሰች ፣ የተራቡትን ያጎረሰች፣ የነገ ህፃናቶቿን የደገፈች፣ተማሪዎቿን ያስታወሰች፣ ማዕድ ያጋራች፣ የኑሮን ጫና ለማቃለል ሸክምን የተጋራች ፣ሌማት እንዲሞላ ያበረታታች... ብዙ ብዙ ቢጠቀስላት ቢያንሳት እንጂ የማይበዛባት፡፡

ዛሬም ከተማችን የተያዘችው ጎዳና ብሩህ መሆኑ ይታያል.... የነገ ትውልድን ጭምር በማሰብ እየተጣሉ ያሉ መሰረቶች የነገን ብሩህነት የሚናገሩ ናቸው፡፡ አዲስ አበባችን እንደመልካም ስሟ አዲስና አበባ ትሆን ዘንድ በተጀመረው ሁሉን አቀፍ ጥረት አሻራችንን እናኑር ፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.