“በሳይንስና ፈጠራ የተካነ ትውልድ ለተምሳሌታዊ ሀገር” በሚል መሪ ሀሳብ ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ 2 ቀናት የሚካሄደውን 11ኛው ከተማ አቀፍ የሳይንስ ፈጠራ ስራ አውደ ርዕይ አስጀምረናል።ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የዛሬው የሳይንስ ፈጠራ ስራ አውደ ርዕይ ዋነኛ ዓላማ ተማሪዎች በንድፈ ሀሳብ የተማሩትን በተግባር የሚያሳዩበት፣ የውስጥ ተሰጥዖዋቸውን የሚገልጹበት፣ ለሰሯቸው የፈጠራ ስራዎች የሚበረታቱበት፣ በትብብር የመስራት ልምድ የሚለዋወጡበት ትልቅ መድረክ መፍጠር ነው።
እውቀት ችግሮችን ደጋግሞ ማውራት ሳይሆን ለችግሮች መፍትሄ ማፍለቅ እና ችግርን ወደ ድል መቀየር ስለሆነ፣ ከተማችንን የሳይንስና ፈጠራ ማዕከል ለማድረግ ሰፋፊ ስራዎች በመስራት ውጤቱንም በተጨባጭ ማየት የተጀመረበት ወቅት ላይ ደርሰናል። ይህ ውጤታማ ጅምሮ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሀላፊነትታውን በአግባቡ መወጣት ይኖርባቸዋል።
ዛሬ የፈጠራ ስራችሁን ያቀረባችሁ ተማሪዎችና መምህራን፣ የፈጠራ ስራችሁ አድጎና በልጽጎ ለከተማችን፣ ለሀገራችን ብሎም ለዓለም የሚተርፍ በረከት ሊሆን እንደሚችል ትልቅ ተስፋ ሰንቀናል፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.