በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ "ሳሪስ አዲስ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ "ሳሪስ አዲስ ሰፈር" ግንባታው የተጠናቀቀው ዘመናዊ የስፖርት ሜዳ አገልግሎት መስጠት ጀመረ

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ​በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 "ሳሪስ አዲስ ሰፈር" ግንባታው የተጠናቀቀው እና በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ዘመናዊ የስፖርት ሜዳ ተገንብቶ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

​ዛሬ ሚያዚያ 17 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደው ደማቅ የምርቃት ስነ-ስርዓት ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ፣ የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ካባ መብራቱ፣ የክፍለከተማው እና የወረዳ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የስፖርት ቤተሰብ ነዋሪዎች ተገኝተው ሜዳውን መርቀው ከፍተዋል።

​በማስ ስፖርት እና በአካባቢው ነዋሪዎች ደማቅ ተሳትፎ የታጀበው የምረቃ ፕሮግራሙ፣ መሰረተ ልማቱ ለአካባቢው ወጣቶች ስፖርታዊ እንቅስቃሴ እና ለጤናማ ማህበረሰብ ግንባታ ጉልህ ፋይዳ ያለው መሆኑን ስለማሳየቱ የክፍለ ከተማው ኮሚኒኬሽን ለኤ ኤም ኤን ዲጂታል በላከው መረጃ አመላክቷል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.