የራስ ኃይሉ የስፖርት፣ ትምህርትና ስልጠና ማዕከ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የራስ ኃይሉ የስፖርት፣ ትምህርትና ስልጠና ማዕከልን ዓለም አቀፍ ውድድሮችን ማካሄድ በሚያስችል ደረጃ በማደስ እና ተጨማሪ መሰረተ ልማቶችን በማሟላት ወደ አገልግሎት እንዲገባ አድርገናል።

ማዕከሉን ቀደም ብሎ መርቀን አገልግሎት መስጠት ካስጀመርን በኋላ  ባጋጠመው የቴክኒክ ችግር ምክንያት አገልግሎቱ ተቋርጦ ቆይቷል። የቴክኒክ ችግሩ እንዲፈታ ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት እና ዓለም አቀፍ ደረጃውን እንዲያሟላ የሚያስችሉ ተጨማሪ መሰረተ ልማቶች እንዲካተቱለት በማድረግ አገልግሎቱን በድጋሚ እንዲጀምር አድርገናል።

ዓለም አቀፍ የኦሎምፒክ ስታንዳርድን የተጠበቀ የመዋኛ ገንዳዎች፤ ሁለገብ ጅምናዚየም፤ የቅርጫት ኳስ፣ የእጅ ኳስ፣ የቮሊ ቦል፣ የቦክስ፣ የማርሻል አርት ውድድሮችን ማካሄድ የሚያስችሉ መሰረተ ልማቶች፤ የሚዲያ ማዕከል፤  የቴኒስና የእግር ኳስ ሜዳዎች፤ ካፍቴሪያ እና ሱቆችን እንዲሁም መናፈሻ እና የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎችን አካቶ የያዘ ዘመናዊ የስፖርት ማዕከል ነው።

በአካልም በአዕምሮም ዳብሮ የተገነባ ሀገር ተረካቢ ትውልድን ለመገንባት በሰነቅነው ራዕይ በከተማችን የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን እና የስብዕና መገንቢያ ማዕከላትን በማስፋፋት ህጻናት እና ታዲጊዎች ስልጠናዎችን እና ልምምዶችን እንዲያገኙ በስፖርት የዳበሩ፣ ጤናቸው የተጠበቀ እና ተወዳዳሪ ብሎም አሸናፊ እንዲሆኑ የሚያስችሉ ተግባራት ተጠናክረው ቀጥለዋል።

ማዕከሉ ከዛሬ ጀምሮ ዓለም አቀፍ ውድድሮችን፣ ልምምዶችን እና ስልጠናዎችን ጨምሮ  በተሟላ መልኩ አገልግሎት መስጠት የጀመረ በመሆኑ ተገልገሉበት፣ ጠብቁት፣ ተንከባከቡት።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይበርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ለተጨማሪ መረጃ👇🏻👇🏻👇🏻

https://linktr.ee/Addis_Ababa_Communication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.