የከተማ አስተዳደራችንን የ2018 በጀት ዓመት የ9 ወራት ስራዎች አፈፃፀም ግምገማ ማካሄድ ጀምረናል።
በበጀት ዓመቱ በእቅድ ከያዝናቸው ተግባራት 96 በመቶ መፈፀም ችለናል።
ለሁለት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው የግምገማ መድረክ በበጅት ዓመቱ ለመፈፀም ካቀድናቸው ውስጥ በ9 ወራት በጥብቅ ክትትል የተከናወኑትን የምንገመግምበት እና በቀሪ ወራት የትኩረት ማዕከል አድርገን የምንፈፅማቸው በመልካም አስተዳደር ተለይተው ያልተመለሱትን ምላሽ በመስጠት ማጠናቀቅ፣ የኑሮ ውድነትን የሚያባብሱ ችግሮችን በመቀነስ የዋጋ ንረትን መከላከል፣ የገበያ ማዛባት ችግሮችን መከላከል፣ ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በመሶብ ዲጅታል የአንድ ማዕከል የመንግስት አገልግሎት የጀመርነውን ውጤታማ ስራ በቀሪ ወራት በተሟላ ሁኔታ በማጠናቀቅና ወደ ስራ ማስገባት እንዲሁም ቀሪ አገልግሎቶችን ዲጅታላይዝ አድርጎ ወደ መሶብ ማስገባት፣ ተጀምረው በዚህ ዓመት መጠናቀቅ ያለባቸውን ፕሮጀክቶች በፍጥነትና በጥራት ማጠናቀቅ የአፈፃፀም ግምገማ ማዕከላችን ይሆናሉ።
ባለፋት አምስት ዓመታት የእቅድ አፈፃፀማችን ከ90 በመቶ በላይ እያደገ መጥቶ በ2018 ደግሞ 96 በመቶ የደረሰበት ውጤታማ አፈፃፀም መኖሩን በመገምገም፣ ይህንን እያደገ የመጣ የመፈፀም ልምድ አጠናክረን መቀጠል እንድንችል በትኩረት እንገመግማለን ።
በተጨማሪም 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍትሃዊ፣ ነፃ፣ ተዓማኒና ገለልተኛ ሆኖ እንዲከናወን ሁሉም አመራራችን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ትልቅ ሃላፊነት መወጣት እንዲችሉ የግምገማ አቅጣጫን አስቀምጠናል።
የነበሩ ጥንካሬዎችን ማስቀጠል፣ ጉድለቶችን በመሙላት በቀሪዎች ወራት በላቀ መፈፀም የግምግማችን ማዕከል ይሆናል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ለተጨማሪ መረጃ👇🏻👇🏻👇🏻
https://linktr.ee/Addis_Ababa_Communication
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.