የሞዛምቢክ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ክቡር ዳንኤል ፍራንሲስኮ ቻፖ ወደ ኢትዮጵያ እንኳን በደህና መጡ።
ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ፣ የብዙ ጸጋዎች ባለቤት ሀገር እንደመሆኗ፤ አጋሮቿን ጸንቶ በቆየውና በጋራ መሰረቶች ላይ ማዕከል ባደረጉ የወል እድገትን ለማንበር ክንዶቿን ዘርግታ ትቀበላለች!
ከእውነተኛ አጋርነታችን የሚቀዳ፤ በጋራ መከባበር ላይ የተመሰረተ፣ በላቀ ርዕይ የተሞላ ዕድገትንና ለውጥን ለሚሹ ሁሉ ኢትዮጵያ መድረሻ ብቻ ሳትሆን፤ ሁለተኛ ቤታቸው መሆኗን እናረጋግጣለን።ክቡር ፕሬዝደንት ዳንኤል ፍራንሲስኮ ቻፖ ቆይታዎ ለጋራ ስኬትና ለዘላቂ ወዳጅነት መሠረት የሚጥል ውጤታማ እንዲሆን እመኛለሁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.