አዲስ አበባ የዓለም አቀፉን "ሲቲ ማውንቴን ባይክ ኤሊሚኔተር ፕሮ ሊግ" ልታስተናግድ ነው
የዓለም አቀፉ የብስክሌት ሕብረት (UCI) ዕውቅና የሰጠውና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተወዳጅነት ያለው "ሲቲ ማውንቴን ባይክ ኤሊሚኔተር ፕሮ ሊግ" በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው።
ይህ ከመላው ዓለም የተውጣጡ ምርጥ ብስክሌተኞች የሚሳተፉበት ታላቅ ውድድር የፊታችን ሚያዝያ 24 እና 25 ቀን 2018 ዓ.ም በፒያሳ አድዋ ድል መታሰቢያ ዙሪያ የሚከናወን ይሆናል።
ውድድሩ በዓለም አቀፍ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በቀጥታ የሚተላለፍ ሲሆን፣ ከ20 ሚሊዮን በላይ ተመልካቾች ይከታተሉታል ተብሎ ይጠበቃል።
አዲስ አበባ እንዲህ ያሉ ዓለም አቀፍ ስፖርታዊ ውድድሮችን ለማስተናገድ ተመራጭ መሆኗ፣ በከተማዋ በስፋት እየተገነቡ ያሉት ዘመናዊ የስፖርት መሠረተ ልማቶች ውጤት መሆኑ ተገልጿል።
የከተማ አስተዳደሩ የስፖርት ዘርፍ ለኢኮኖሚ ግንባታና ለትውልድ ዕድገት ያለውን ሚና ከግምት ውስጥ በማስገባት የጀመራቸው የልማት ሥራዎች፣ ከተማዋን የዓለም አቀፍ ስፖርታዊ ኩነቶች ማዕከል እያደረጓት ይገኛል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.