”የማህበራዊ ልማት እመርታ ለሀገር ግንባታ’’
”የማህበራዊ ልማት እመርታ ለሀገር ግንባታ’’ በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀውና በማህበራዊ ዘርፍ ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ዐበይት ውጤቶች የቀረቡበት የምክክር መድረክ ተገኝቼ ሃሳቤን አጋርቻለው።
የማህበራዊ ዘርፍ ግንባታ እንደ ሌሎች መሠረተ-ልማቶች ውጤቱ ወዲያው የሚታይና የሚጨበጥ ባይሆንም፣ ለሀገር ዘላቂና ወሳኝ መሰረት የሚጥል ነው። ኢትዮጵያ በሚገጥሟት ተግዳሮቶች ሳትገደብ ከሚገመተው በላይ በከፍተኛ ፍጥነት እየተገነባች ሲሆን፣ ምንም እንኳ የዐቅም ውስንነቶች ቢኖሩብንም ለማሻሻል ያልተሞከረ የማህበራዊ ዘርፍ የለም።
በዘርፎች የታለመው ሁሉ በተግባር እንዲተረጎምና ተገቢውን ዓላማቸውን እንዲያሳኩ ብዙ ሥራ ይጠበቅብናል። ስለሆነም አንድ እጅ ብቻውን ማጨብጨብ አንደማይችል ሁሉ፤ መንግሥት የሚጀምራቸውን ሥራዎች ሌላው የማህበረሰብ ክፍል እንደ አንድ ባለ ድርሻ ኃላፊነት ወስዶ በጋራ መቆም ይኖርብናል።"
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ባለፉት ስምንት የለውጥ ዓመታት በሚኒስትር መስሪያቤታቸው የተመዘገቡ ዐበይት ስኬቶችን አቅርበዋል።
በዚህም ዘርፉ ከለውጡ በፊት ሲቸገርበት የነበሩ መጠነ ሰፊ ክፍተቶችን በመለየት ፈጣን መፍትሔ በመስጠት ሰፊ ስኬቶችን አስመዝግቧል።
ከተገኙ ስኬቶች መካከል ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፦
የፖሊሲና የህግ ማዕቀፎችን በማዘጋጀት የዜጎችን መብት ጥበቃ፣ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ። አደረጃጀቶችን በመደገፍና በማጠናከር መብትና ግዴታ በማወቅ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፣ የአቅመ ደካማ ዜጎችን የመደገፍና የማገዝ ባህል ማሳደግ ጥቂቶቹ ናቸው።
እነዚህ ስኬቶች ቁጥር ብቻ ሳይሆኑ በተጨባጭ 4,330,948 የሚሆኑ ወጣቶች እና 26,845,686 ሴቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የተቻለበት ትልቅ ስኬትም ጭምር እንጂ! ከዚህ በተጨማሪም የሴቶችንና ወጣቶችን የፖለቲካ ተሳትፎን ከማሳደግ አኳያ ሰፊ ስራ ተሰርቶ ተጨባጭ ስኬቶች ተመዝግበዋል።
በተጨማሪም ዘርፉ ካስመዘገባቸው ስኬቶች መካከል የማህበራዊ አገልግሎት ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ አንዱና ዋነኛው ሲሆን በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋ ተጋላጭ ሆነው ድጋፍ የተደረገላቸው ዜጎች፣ ከጎዳና ላይ የተነሱ ዜጎች፣ የተሀድሶ አገልግሎት ያገኙ አካል ጉዳተኞች፣ በማህበረሰብ እንክብካቤ ጥምረቶች የተሰበሰበ ሀብት ዋነኞቹ ስኬቶች ናቸው።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.