ለኑሮ አመቺ ያልነበሩ አፍርሰን በአጭር ጊዜ መልሰን የገነባናቸውን እና ያደስናቸውን 907 ቤቶች እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ ብለን ዛሬ ለነዋሪዎች አስተላልፈናል። አዳዲስ ግንባታዎችንም አስጀምረናል።
አርጅተው በመፍረስ ላይ የነበሩ ጎስቋላ ቤቶችን አፍርሰን ለዘመናዊ አኗኗር አመቺ በሆነ መልክ እዚያው በነበሩበት ቦታ ላይ መልሰን የገነባነው በርካታ ልበቀና ባለሃብቶችን በማስተባበር ነው።
ጥሪያችንን በመቀበል ለወገኖቻችሁ በመድረስ ማህበራዊ ኃላፊነታችሁን የተወጣችሁ የከተማችን ባለሃብቶችን በተጠቃሚ ነዋሪዎቹ እና በራሴ ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ።
ነዋሪዎቻችንም የዚህ እድል ተጠቃሚ ስለሆናችሁ እንኳን ደስ አላችሁ! ማህበራዊ ፍትህ የነገሰባት አዲስ አበባን የመገንባት ስራችን ተጠናክሮ ቀጥሏል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.