"ዛሬ በግሉ ዘርፍ አግሮ ኢንዱስትሪ የወተት ምርቶች በማቀነባበር በምርት አይነት፣ በብዛት እና ጥራት የወተት እና የወተት ምርቶችን ለከተማችንና በመላው ሃገሪቱ ለተጠቃሚዎች በስፋት ለማቅረብ ነባሩን የላሜ ዴይሪ አምራች ኢንዱስትሪ ተደራሽነቱን የሚያሰፋ ተጨማሪ የወተት ማቀነባበሪያ ፋብሪካ መርቀናል
ሃገራችን በርካታ የቀንድ ሃብት ያላት ቢሆንም በእሴት ሰንሰለት እና በምርታማነት ውስንነት ምክንያት የወተት አቅርቦቱ ላይ አሁንም እጥረት ያለበት መሆኑ ይታወቃል። ይሄ ደግሞ ወተት እያገኙ ማደግ የሚገባቸውን ህጻናትና አምራቹን ዜጋ የሚጎዳ ነው። ዛሬ በላሜ ዴይሪ ያየነው በምርት ብዛት እና አይነት በዘመናዊ መንገድ ጤናማ እና ከ6 ወራት በላይ ያለማቀዝቀዣ የሚቆይ የወተት ምርቶች ማምረት መጀመሩ ችግሩን የሚያቃልል ነው ።
ከዚህም በተጨማሪ ለአርሶ አደሮቻችንም ያመረቱትን ምርት ለገበያ በጥራት ማቅረብ እንዲችሉ የገበያ ትስስር የመፍጠር ጥሩ ጅማሮ ተጠናክሮ መቀጠል ይገባዋል።"
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.