ዛሬ በከተማችን አዲስ አበባ 7ኛው አገራዊና ከተ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ በከተማችን አዲስ አበባ 7ኛው አገራዊና ከተማ አቀፍ ጠቅላላ ምርጫ የብልጽግና ፓርቲን ዓላማና ግብ የሚደግፍ፣ የፓርቲውን የምረጡኝ ቅስቀሳ የሚያጎላ ታላቅ የድጋፍ ሰልፍ በደማቅ ሁኔታ ተካሂዷል።

ምርጫ ለአንድ አገር ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ መሠረት ነው።
 
የሕዝብ ሉዓላዊነት የሚገለጽበትና ሕዝብ በድምፁ መንግሥት የሚመሠርትበትም ሂደት ነው።
ያለ ምርጫ መንግስት መመስረት አይቻልም። ያለ ህዝብ ተሳትፎና  ውሣኔም አይሳካም። ብልፅግናም ሊቀጥል የሚችለው በህዝብ  ውሣኔ ብቻ ነው። ህዝብ የመወሰን ሥልጣን ከተረጋገጠለት እና ህዝባችንም ዴሞክራሲያዊ መብቱን ተጠቅሞ ከወሰነ የኢትዮጵያን ብልፅግና የሚያቆመው አይኖርም።
 
ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ የመገለል፣ የመጨፍለቅ ወይም  የበላይነት የሚነግስበት እድል የለም ። በሁላችን፣ ከሁላችን፣ የሁላችንም የሆነች ሃገር እየገነባን ነው ። 
በከተማችን አዲስ አበባ ማንንም ያልዘነጋ አካታች የሆነ ልማት እየሠራን እንገኛለን ።አዛውንቶች እፎይ እንዲሉ፣ ህጻናት ቦርቀው እንዲያድጉ፣ ወጣቶች ተገቢውን ሥራ አግኝተው  በአካል እና በአዕምሮ ጎልብተው እንዲያድጉ ህልማቸውን እንዲኖሩ የስፖርት ማዘውተሪያዎች ገንብተናል።
 
 የከተማችንን ጎስቋላ ገጽታ ለመቀየር በሰራነው ስራ 74 በመቶ የነበረው የጭቃ ቤት ወደ 30 በመቶ ዝቅ አድርገናል።

 ጨለማ የነበሩ የአዲስ አበባ ጎዳናዎች ዛሬ በርተዋል፤ ጠባብ ጎዳናዎች ሰፍተዋል። ለህዝባችን ምቾትን የሚጨምሩና ክብርን የሚጠብቁ እንዲሁም ጤናው እንዲጠበቅ የሚያስችሉ ንጹህ፣ አረንጓዴ ውብ ከተማ በስፋት ገንብተናል። ከአፍሪካ አስር ንጹህ ከተሞች አዲስ አበባ አንዷ እንድትሆንም አድርገናል።
እኛ በምርጫ ወቅት ብቻ ህዝብ ትዝ አይለንም። ህዝብ ውስጥ ነበርን፤  ከህዝብ ጋር ነን። መንግስት ከመሆናችን በፊት ለህዝብ ታግለናል፣ ህዝባችን እንድናገለግለው ዕድል ከሰጠን በኋላም ችግሩን እየተረዳን በርካታ መፍትሔ ሰጥተናል። 
 
በ7ኛው ዙር ምርጫም ለሕዝባችን ቃል የምንገባው፣ ከተመረጥን ዘላቂ ሰላምንና  ሁለንተናዊ ብልፅግናን ሌት ተቀን በመሥራት ያለምንም መሸራረፍ እንደምንፈጽም ነው።
የብልፅግና ፓርቲ ማኒፌስቶ የትላንትን መልካም አሻራዎች ማስቀጠያ ፣ የከረሙ ችግሮች ማከሚያ፣ ዛሬን በአግባቡ መጠቀሚያ፣ ነገን መተለሚያና ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት አገር ማሻገሪያ ቃል ኪዳን ነው። 
 
ብልፅግናን መምረጥ ከድህነትና ከኋላ ቀርነት ወጥቶ አስተማማኝ መጻኢ ዕድልን ለመገንባት መወሰን፤ ብልፅግናን መምረጥ እውነተኛ ዴሞክራሲን መምረጥ ነው። 
የምርጫ መወዳደሪያ ምልክታችን የሆነው የስንዴ ነዶም የመደመር፣ የአንድነት፣ የተባብሮ መሥራት፣ የምርታማነት፣ የተምሳሌትነት፣ የልዕልና እና የሉዓላዊነት መገለጫ ነው። ይህም በሁላችን፣ ከሁላችን፣ ለሁላችን ብልፅግናን የምናረጋግጥበት ምልክታችን ነው።
 
ስለሆነም፣ ብልፅግና ቃሉን ይጠብቃል፤ ቃሉን ይፈጽማል፤ ሕዝቡን የሉዓላዊ ሥልጣን ባለቤት ያደርጋል!
እስከ ዛሬ ላስመዘገብነው ውጤት ከጎናችን ያልተለያችሁን፤ የደገፋችሁን እንዲሁም ዛሬ ማልዳችሁ በታላቅ ሞራል ወጥታችሁ ድጋፋችሁን የገለፃችሁልን ውድ የከተማችን ነዋሪዎች ፈጣሪ ያክብርልን፤ እጅግ አድርገን እናመሰግናለን። ዳግም ብትመርጡን ከዚህ በላይ በትጋት፣ በታማኝነት እና በቅንነት ልናገለግላችሁ ቃል እንገባለን።
 
ብልፅግናን ይምረጡ!
 
ኢትዮዽያን ወደ ተምሳሌት አገር ! 
 
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ !!


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.