ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤ በዐል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የትንሳኤ በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ሁሉ በመስቀል ላይ እስከሞት ድረስ ራሱን አሳልፎ በመሰጠት ወደር የለሽ ፅኑ ፍቅር ያሳየበት እና እንዲሁም ለበደሉት ሳይቀር ይቅርታና ምህረትን የሰጠበት፣ ሞትንም ድል ያደረገበት መታሰቢያ በዓል በመሆኑ እኛም፣ እርስ በርሳችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሁሉንም ሰው በመውደድ፣ በይቅርታ፣ በምህረትና በመርዳዳት እንድንኖር ፈጣሪ ይርዳን። በዚህ በኩል ለተዳከሙ እሴቶቻችንም ትንሳኤ ይሁን።
በዓሉ የፍቅር፣ የሰላም፣ የይቅርታ፣ የምህረት፣ የመርዳዳት፣ የደስታ እና አብሮነታችን የሚጠናከርበት ይሁን።
በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ፣ መልካም በዓል
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.