የአራት ዓመታት ተከታታይ ጥረት እና የሚጨበጥ ው...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአራት ዓመታት ተከታታይ ጥረት እና የሚጨበጥ ውጤት!

በዘንድሮው “ኢትዮጵያ ታምርት” ኤክስፖ ላይ የሀገራዊ ርዕያችንን ተጨባጭ ስኬት መመልከት ትልቅ ክብር ነው። ውጤት ተኮር አመራራችን ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ የኢንዱስትሪ መስፋፋት ተንጸባርቋል። ይኸውም የአምራች ኢንዱስትሪዎችን አማካይ የማምረት አቅም ከ47 በመቶ ወደ 67 በመቶ ከፍ በማድረግ፣ ባለፉት አራት አመታት ከ2,800 በላይ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንቶችን መሳብ የተቻለ ሲሆን፤ በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ዘጠኝ ወራት ውስጥ ብቻ በሀገር ውስጥ ተኪ ምርት ከ4.85 ቢሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ በማዳን ተረጋግጧል። ኤክስፖው ከመላው የሀገሪቱ የተወጣጡ ንቁ አምራቾችን እና ስታርትአፖችን በጨመረ ዐቅም በአንድነት አሰባስቧል።

‎በጋራ በመሆን ይህንን ጠንካራ መነቃቃት በማስቀጠል፣ ለሚመጣው ትውልድ ጽኑ፣ በኢንዱስትሪ የበለጸገች እና ራሷን የቻለች ኢትዮጵያን እንገነባለን።  
‎ 
‎ታላቅ የነበርን ይበልጥም ታላቅ እንሆናለን!

 
Four Years of Sustained Effort and Measurable Progress!
 
It is truly an honor to witness the tangible realization of our national vision at this year's "Made in Ethiopia" Expo. Our results-driven governance is reflected in unprecedented industrial expansion, highlighted by average production capacity utilization soaring from 47% to 67%, the attraction of over 2,800 domestic and foreign direct investments over the past four years, and more than $4.85 billion in foreign exchange saved through import substitution in the first nine months of the 2018 fiscal year alone. 
 
This expo unites hundreds of dynamic enterprises and innovative startups from across the nation. By working together and sustaining this powerful momentum, we will build a resilient, industrialized, and self-reliant Ethiopia for generations to come.
 
We Were Great and We Shall Be Even Greater!
 
#EthiopiaDelivers #MadeInEthiopia


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.