በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው "የሲቲ ማውንቴን ባይክ ኤሊሚኔተር ፕሮ ሊግ (City Mountain Bike Eliminator Pro League)” ውድድር በኢትዮጵያ - በአዲስ አበባ አስተናጋጅነት ተካሂዷል።
አዲስ አበባ በታሪኳ አዲስ ምዕራፍ እየከፈተች ነው።
መነሻውንና መድረሻውን የመላው ጥቁር ህዝቦች ታሪክ በሆነው የአድዋ ድል መታሰቢያ ያደረገ "የሲቲ ማውንቴን ባይክ ኤሊሚኔተር ፕሮ ሊግ (City Mountain Bike Eliminator Pro League)” ውድድር ከ24 በላይ ሃገራት በመጡ ፕሮፌሽናል ተወዳዳሪዎች መካከል በከፍተኛ ፉክክር እና ወኔ የተካሄደ እጅግ ደማቅ ውድድር ነው።
ስፖርት ከዓለም ጋር የምንገናኝበት፣ የምንግባባበት እና ትብብርን የምናጠናክርበት አንዱና ትልቁ ዘርፍ ነው።
መንግሥታችን ለስፖርት ዘርፍ ያለው እይታ በመቀየሩ ስፖርት ወዳዱን ማህበረሰባችንን ከዓለም የስፖርት ውድድሮች ጋር ለማያያዝ በሰራነው ሥራ በሁለት ሳምንታት ብቻ 3 ዓለም አቀፍ ውድድሮችን ማዘጋጀት ችለናል።
ይህ ውድድር የአፍሪካ ዲፕሎማሲ መዲና እና በጥቁር ህዝቦች የድል ታሪክ መታሰቢያ እንዲካሄድ ለመረጣችሁ እና ቀጣይ ዓመትም እዚሁ እንደሚካሄድ ላረጋገጣችሁልን የዓለም አቀፉ የብስክሌት ህብረት (UCI)፣ ለዝግጅቱ ስኬት ሌት ተቀን ለደከማችሁ የስፖርት አመራሮችና አካላት በሙሉ በከተማ አስተዳደሩ ስም የላቀ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
በተጨማሪም በከፍተኛ እንግዳ ተቀባይነት፣ ጨዋነት እና ስፓርት አድናቂነት ድጋፋችሁን ለገለፃችሁ የከተማችን ነዋሪዎችም የላቀ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.