"ትንሳዔ በዓልን በአዲስ መንፈስ ፤ በአዲስ ህይወት "የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒካሽን ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ የበጎ ፈቃድና የማዕድ ማጋራት ስራን በመደገፍ የ4 አቅመ ደካማ አባዎራዎች ቤት በአዲስ መልክ ገንብቶ በትንሳዔ በዓል ዋዜማ ለነዋሪዎቹ አስረከበ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በታላቅ ትጋት እየሰራ ያለዉን የበጎ ፍቃድ እና ማዕድ ማጋራት ተግባር የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ለህዝቡ ግንዛቤ ከማስጨበጥ በተጨማሪ በአራዳ ክፍለ ከተማ በአዲስ መልክ ተገንብተዉ የተጠናቀቁ የአራት አቅመ ደካማ አባዎራዎች ቤቶችን የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ እናትዓለም መለሰ ተገኝተዉ አስረክበዋል፡፡
ለበዓሉ መዋያ የሚሆን በግ፤ዘይትና ዱቄት በመስጠት ቢሮዉ አጋርነቱን ገልፃል፡፡
የበጋና የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ህብረተሰቡን በማስተባበር የተጀመረዉ ስራ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ቢሮዉ ገልጿል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.