ይህን የአፍሪካዉያንን ዘመን እዉነታ እኛ አፍ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ይህን የአፍሪካዉያንን ዘመን እዉነታ እኛ አፍሪካዉያን ልንማርበትና ለተቀረዉ የዓለም ማህበረሰብ የምናስተዋዉቅበት ታሪካዊ አጋጣሚን አዲስ አበባ ፈጥራልናለች ።" የአፍሪካ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪ ጎብኚዎች

ከ30 የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ 321 ሚሊዮን የሚጠጋ ተከታይ ያሏቸዉ 61 የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች

የመዲናዋን ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች በዛሬዉ ዕለት ተዘዋዉረዉ ጎብኝተዋል።

አርቴፊሻል ኢተለጀንስ ሴንተር፣ጉለሌ የእንጀራ ማዕከል፣ ፣አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዘየም፣የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማቶች፣የመሠረተ ልማት ዝርጋታዎች፣አራዳ ፓርክ፣አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል፣ካሳንቺስ የሚገኘዉ ስፖርት ፖርክ እና ሌሎች ዘርፈ ብዙ የልማት ስኬቶች የተጎበኙ ሲሆን የሀገራችን ታዋቂ የሶሻል ሚዲያ ተፅእኖ ፈጣሪዎች ጭምር በጉብኝቱ ተሳትፈዋል።

ጉብኝቱ በመዲናችን አዲስ አበባ የሚካሔደዉ የመጀመሪያ የአፍሪካ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ (ASMIS 2026) አንዱ አካል መሆኑና ይህም የመዲናችንን እና የአፍሪካ እውነተኛ ገጽታ ለዓለም ለማስተዋወቅና የዲጂታል ትርክቱን በባለቤትነት ለመምራት ያለመ ነዉ ተብሏል።

በጉብኝቱ ወቅት ያነጋገርናቸዉ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅእኖ ፈጣሪዎች እንደገለፁት በአዲስ አበባ እና በዙሪያዋ ተዘዋዉረን ያየናቸዉ የልማት ስራዎች እዉነትም የኢትዮጽያ ሁለተናዊ ፈጣን እድገት ለራሷ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካዉያን ኩራት ለተቀረዉ ዓለም ጭምር የአፍሪካዉያን የቀጣይ ጉዞ የተመላከቱበትና በራስ አቅም ሰርቶ መለወጥ መቻልን በተጨባጭ ያረጋገጥንበት የአፍሪካዊነት መገለጫ ዘመን ነዉ ሲሉ ገልፀዋል።

የአንድ ሀገር ፈጣን እድገት እና ለዉጥ መሠረቱ የመንግስት እና የህዝብ ጥምረት፣ቁርጠኝነትን የተላበሰ የአመራር ብቃትና ትጋት እንዲሁም ፀጋዎችን እና ቴክኖሎጁን መጠቀም መቻል ነዉ ያሉት ጎብኚዎቹ የሠዉ ዘር መገኛ እና የሁላችን ቤት በሆነችዉ ዉብ ፣ፅዱ ፣አረንጎዴ ለበስ ተመራጭ እየሆነች ባለችዉ ከተማ አዲስ አበባ ይህንኑ ማየት መቻላችን በእጅጉ አስደስቶናል ብለዋል።

ይህን የአፍሪካዉያንን ዘመን እዉነታ እኛ አፍሪካዉያን ልንማርበትና ለተቀረዉ የዓለም ማህበረሰብ የምናስተዋዉቅበት ታሪካዊ አጋጣሚ በመሆኑ ሙያችንን በመጠቀም የተጣለብንን አፍሪካዊ ኃላፊነት መወጣት ይጠበቅብናል ሲሉም ገልፀዋል።

በመጨረሻም በዚች ዉብ ፅዱ እና አረንጓዴ ከተማ ፣በመንግስትና በህዝቦቿ አቀባበልና እንግዳ አክባሪነት መማረካቸዉን የገለፁት የአፍሪካ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ለተፈጠረላቸዉ እድልና የጋራ እድገት በአፍሪካዉያን እና በመላዉ ተከታዮቻቸዉ ስም ልባዊ ምስጋናቸዉን አቅርበዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.