የነዋሪዎችን ማህበራዊና አኢኮኖሚያዊ ፈተናዎችን...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የነዋሪዎችን ማህበራዊና አኢኮኖሚያዊ ፈተናዎችን ለማቃለል የከተማ አስተዳደሩ ዘላቂ የልማት መፍትሄዎችን እየተገበረ ነው፡- አቶ ጃንጥራር አባይ

የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ማህበራዊና አኢኮኖሚያዊ ፈተናዎችን ለማቃለል ከተማ አስተዳደሩ ዘላቂ የልማት መፍትሄዎችን እየተገበረ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የአኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ገለፁ። 

ምክትል ከንቲባው የትንሳዔ በዓልን ምክንያት በማድረግ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 05 እንደ አዲስ የተገነቡ የአቅመ ደካማ እና የሀገር ባለውለታ ቤቶችን መርቀው ለባለቤቶቹ አስረክበዋል። 

በአቅም ማጣት ምክንያት ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ማህበራዊ ችግር በትብብር የመፍታት የአዲስ አበባ ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። 

በመሰረታዊነትም የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን ፈተናዎች ለማቃለል የመሰረተ ልማት ስራዎችን ዛሬ በወረዳ 01 እና 05 እንደመረቅናቸው ቤቶች በሁሉም መስክ የልማት ስራዎቻችንን በማጠናከር በዘላቂነት የዜጎችን ጥያቄ ለመፍታት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በርካታ ነዋሪዎችን በምቾት የሚያስተናግዱ ልማቶች እየተከናወኑ ይገኛልም ብለዋል። 

በዚሁ ሂደትም አስቸጋሪ ህይወትን እየመሩ ያሉ የከተማ ነዋሪዎች ማህበራዊ ችግር ለማቃለል የተጀመረው የበጎ ፈቃድና የሰው ተኮር ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉም ብለዋል። 

የአቅመ ደካሞችን ቤት በማደስና መልሶ በመገንባት በጎ ተግባር ውስጥ ተሳትፎ ላደረጉ ባለሀብቶችና መንግስታዊ ተቋማት ምክትል ከንቲባው ምስጋና አቅርበዋል። 

በትንሳዔ በዓልም የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ከዚህ ቀደም ሲያደርጉት እንደነበረው ያላቸውን ከአቅመ ደካሞች ድጋፍ ከሚፈልጉ ዜጎች ጋር በጋራ እንዲያሳልፉም ጥሪ አቅርበዋል። 

የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሀኑ ረታ በበኩላቸው ከወረዳ 01 እና 05 በተጨማሪ በሁሉም ወረዳ በትንሳዔ በዓል ዋዜማ ሙሉ በሙሉ ፈርሰው የተሰሩ 150 ቤቶች በክፍለ ከተማው በሚገኙ ልበ ቀና ባለሃብቶችን በማስተባበር ተሰርተው ለአቅመ ደካሞች መተላለፋቸውን አስታውቀዋል።

ምክትል ከንቲባው በየካ ክፍለ ከተማ ለሚገኙ የፀጥታ ግብረ ሀይል አባላትም 15 በሬዎችን ለበዓል መዋያ አስረክበዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.