ዛሬ 3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ 3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ አመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤ በመራጭ ተመራጭ ከህዝብ ጋር በተደረጉ ውይይቶች ወቅት ለተነሱ ጥያቄዎችን ምላሽና ማብራሪያ አቅርበናል።

 


ከቤት አቅርቦት ጋር በተያያዘ  ፍላጐትና አቅርበትን ለማጣጣም 5 ስትራተጂዎችን ነድፈን በመንግሥት በጀት፡ በመንግስትና በግል አጋርነት፡ በግል፥ በሪልስቴት እና በግለሰብና ግለሰብ  ቤቶችን እየገነባን እንገኛለን።
በበጀት ዓመቱ በመንግሥት በጀት 50 ሺህ ቤቶችን፥ በመንግሥትና የግል አጋርነት 55 ሺህ በአጠቃላይ 105 ሺህ ቤቶች እየተገነቡ ነው ። አሁን ላይ አፈፃፀማቸው ከ40 እስከ 90% እየተጠናቀቁ ነው። በመንግስት የሚገነቡት ሲጠናቅቁ ቅድሚያ ስጥተን እየቆጠቡ ላሉት የሚተላለፉ ይሆናል።

የኑሮ ውድነት ዓላማቀፍ ክስተት መሆኑ ይታወቃል። ሆኖም በገበያ ማዛባት የኑሮ ውድነት እንዳይባባስ የቁጥጥር ሥርዓተ መዘርጋት፥ የምርት አቅርቦትን ለማሳደግ በብዛትና በጥራት ማምረት፥ተኪ ምርቶችና ማምረት፥  በአምስት መግቢያ በሮች ስድስት የገበያ ማዕከላትን  የእሁድ ገበያዎችን በተለያዩ የከተማው ቦታዎች መስርተን ለነዋሪዎች ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ ችለናል። በተጨማሪም 18 ቢሊዮን ብር ድጎማ በተለያዩ ዘርፎች ላይ ድጎማ በማድረግ የነዋሪዎቻችንን የኑሮ ጫና ለመቀነስ ሰርተናል።

አዲስ አበባን የጤና ቱሪዚም ማዕከል ለማድረግ በሰራናቸው ሥራዎች 4 አዳዲስ ሆስፒታሎች ተገንብተዋል።  9 በመጀመሪያ ሆስፒታል ደረጃ የተገነቡ ጤና ጣቢያዎች ተገንብተዋል። አብዛኛዎቹን ነባሮቹ ሆስፒታሎችን ዘመናዊ፣ ቴክኖሎጂ የተሟላላቸው እና በአልጋ ቁጥርም በእጥፍ እንዲጨምሩ አድርገን አድሰናቸዋል።

የትራንስፓርት አግልግሎት ለማሻሻል በዋናነት የመንገድ መሰረተ ልማቱን የማስፋት ስራ ሰርተናል። የመኪና፥ የብስክሌት እና የእግረኛ መንገዶችን ተለይተው ተገንብተዋል ። የመንገድ ሽፋንን 12.8% ወደ 20.% አሳድገናል።  163000 መኪናዎችን ማቆም የሚችሉ ፓርኪንግ ተገንብተናል። 
 
በከተማችን ለህጻናት ምቹ የሚጫወቱባቸው ከ5ሺህ በላይ የልጆች መጫወቻ ፣እንክብካቤ የሚያገኙበት  ከ1000 በላይ ዴይ ኬር ገንብተን ወደ ስራ አስገብተናል።

ወጣቶች በአእምሮና በአካል የዳበረ   እንዲሆኑ የስፖርት ማዘውተሪያዎች በየሰፈሩ ገንብተናል፥ ትላልቅ ስታዲየሞች እየተገነቡ ነው ። ወጣቶቹን ተወዳዳ ብቁ ለማድረግም በኢኒሼቲቭ ከ3000 በላይ ወጣቶች ላይ ልዩ ስልጠና እየሰጠን እንገኛለን። 
 
ከነጠላ ትርክት ይልቅ አሰባሳቢ ትርክትን ለመፍጠር ለኪነጥበብ ስራዎች መከወኛዎች በስፋት ገንብተናል። በዘርፋም የሰው ሃይል ለማብቃት አሁንም አቅደን የምንሰራ ይሆናል።

74 በመቶ የሚሆነውን የከተማችንን ጎስቋላ ገጽታ ለመቀየር ወደ ውብ ምቹ ከተማ ለማድረግ በሰራነው ሥራ ወደ 30 በመቶ ማድረስ ችለናል። ቆሻሻ አወጋገድ ስርዓትን ለማስተካከል ሰፋፊ የፍሳሽ መስመሮችን ገንብተናል፤ የነበሩትንም አስፋፍተናል። በዚህም  በቀሻሻ አወጋገድ ስርዓት ዓለማቀፍ እውቅና ማግኘት ችለናል። 

በከተማችን መብራት ለማስፋፋት በተሰራው ስራ ጨለማ የነበሩ አካባቢዎች ተገልጠዋል፤ በዚህም ለወንጀል  አጋላጭ የነበሩ አካባቢዎች ተቀይረዋል። የትራፊክ አደጋንም በዚሁ ልክ መቀነስ ችለናል። በቀሩ አካባቢዎችም አቅደን  በስፋት የምንሰራ ይሆናል።

በተግዳሮት ውስጥ  የነበረው  አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል የአዲስ መሶብ አንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎትን በስድስት ማዕከላት ተግባራዊ ማድረግ ችለናል። በዚህም 150 አገልግሎቶች ወደ መሶብ ዲጂታል አንድ ማዕከል በማስገባት ቀልጣፋና ፍትሐዊ አገልግሎት መስጠት ጀምረናል። በአጭር ጊዜ ውስጥም ቀሪ  አምስት ማዕከላት ወደ ሥራ ይገባሉ።

ሙስናና ለአገልግሎት እጅ መንሻ የሚጠይቁትን ለማጋለጥ፥ በሚዲያ በግልፅ ተጠያቂ የማድረግ፤  አስተዳደራዊና በወንጀል በህግ ተጠያቂነትን የማስፈን ስራዎች እየሰራን ነው። እስከ 9ወር ድረስ ባለው የተያዙ ተጠርጣሪዎች 420 ሲሆን፥ አመራር 40፥ ባለሙያ 230፥ የተጠረጠሩበት ወንጀል ተጠቀሚ ሰዎች 150 ሲሆኑ  ሁሉንም እንደየተሳትፎቸዉ ተጠያቂ ተደርገዋል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.