እንኳን ለዓለም አቀፍ የእናቶች ቀን አደረሳችሁ!
የአዲስ አበባ ሴቶች ዛሬ ማልዳችሁ ውቢቷን ቸርችል ጐዳና በመሙላት ለሰጣችሁን ድጋፍ እናመሰግናለን!!!
ዛሬ በዓለም አቀፍ የእናቶች ቀን መላው የከተማችን ሴቶች የተሳተፉበት በ7ኛው ሀገራዊና ከተማ አቀፍ ጠቅላላ ምርጫ የብልጽግና ፓርቲን ዓላማና ግብ የሚደግፍ፣ ታላቅ የድጋፍ ሰልፍ በደማቅ ሁኔታ ተካሂዷል።
ባለፉት 5 ዓመታት በገባነው ቃል መሰረት የሴቶች ተጠቃሚነትንና ቁልፍ ውሣኔ ሰጪነት እንዲረጋገጥ ሰርተን ተሳክቶልናል። የእናቶችን ጫና ለመቀነስ ልጆቻችሁ ያለምንም ሃሳብ ሁሉም ነገር ተሟልቶላቸው እንዲማሩ ከተማ አስተዳደራችን እጅግ ውጤታማ ስራ ሰርቷል።
በአበበች ጎበና የተሰየመ የእናቶችና የህፃናት ሆስፒታል በመገንባት፣ የነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ልህቀት ማዕከል በመገንባት፣ የእንጀራ ፋብሪካዎች ለሴቶች በመገንባት፣ በአጠቃላይ ባለፉት 5 ዓመታት ከፈጠርነው 2 ሚሊዮን የሥራ ዕድል 51 በመቶው ሴቶች እንዲሆኑ በመስራት፣ የሴቶችን አይተኬ ሚና እና ክብር የሚወክል አደባባይ በመገንባት እና የመሳሰሉ የሴቶችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እና ክብር ለማረጋገጥ የተሰራው ስራ ፍሬ አፍርቷል።
አሁንም በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በከተማችን ካቀረብናቸው እጩዎች 54 በመቶ ሴቶች ናቸው። በከተማችን ምክር ቤት ከ40 በመቶ በላይ ሴቶች በመሆናቸው ከዚህ በፊት የነበረውን ተሳትፎ በበለጠ አልቀነዋል። ይህ ደግሞ ለአጃቢነት ሳይሆን የሴቶች ሚና አይተኬ መሆኑን በማመን ነው ።
በ7ኛው ምርጫ ብልፅግናን ስትመርጡ፣ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና ታስቀጥላላችሁ፤ ሰላማችንም ዘላቂ ሆኖ ይረጋገጣል።
የምርጫ ምልክታችን የሥንዴ ነዶ ነው። ልክ እንደ ነዶው ተደምረን፤ ማንንም ያልተወ፣ ማንንም ያልዘነጋ አካታች ልማትን እያረጋገጥን እንቀጥላለን።
ባለፉት 5 ዓመታት የከተማችንን ሠላም በማረጋገጥ፣ ልማትን በማረጋገጥ አብራችሁን ስለነበራችሁ አዲስ አበባ ከልብ ታመስግናችኋለች።
መንገዳችን መደመር፤ መደረሻችን ብልፅግና ነው!
ኢትዮዽያን ወደ ተምሳሌት አገር !
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ !!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.