"አዲሲቷ አዲስ" በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ በሚ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

"አዲሲቷ አዲስ" በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ በሚገኘው የውይይት መድረክ ላይ ጥናታዊ ፅሁፍ ቀርቦ ውይይት እየተካሄደ ነው።

በመዲናዋ የተከናወኑ የልማት ስራዎች የሁሉም አጋሮች ርብርብ የታየበትነው- የዘርፉ ባለሙያዎች።

በአዲስ አበባ የተከናወኑ የልማት ስራዎች የመንግስት እና የህዝብ አጋርነት የታየበት  መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ተናገረዋል ።

የኮሪደር እና የወንዝ ዳር ልማቶች የአዲስአበባን ሁሉን አቀፍ ስርዓት መቀየር ችሏልም ብለዋል።

እነዚህ የልማት ስራዎች ለሴቶች የስራ እድል ተጠቃሚነት፣ የተማሪዎች ምገባ እና አረንጓዴ አሻራ ጋር የተናበቡ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ሁሉም የልማት ፕሮጀክቶች ትልቅ ተሻጋሪ፣ አዳጊ እና ተስፋፊ መሆናቸው ልዩ እንደሚያደርጋቸው አብራርተዋል።

እነዚህ የልማት ስራዎች እኩል ተጠቃሚነትን ያረጋገጡ፣የተቀናጀ መንደር ልማት፣ የህዝብ መገልገያዎችን ያሟሉ ናቸው ብለዋል። የኮሪደር ስራዎች አደጋን በመቀነስ የተሰሩ መሆናቸውንም አመላክተዋል።

አክለውም ፍጥነት እና ጥራትን ማስታረቅ ያስቻለ፣ ጠንካራ የስራ ባህል የታየበት መሆኑን አብራርተዋል።

ባለፉት ሁለት አመታት የተሰሩት የልማት ስራዎች ባለፉት 50 አመታት ከተሰሩት በእጥፍ እንደሚበልጡ ተናግረዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.