በንፋስ ስልክ ላፍቶ ከህጋዊ የልማት ተነሽዎች ጋ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ከህጋዊ የልማት ተነሽዎች ጋር በጥገኝነት ሲኖሩ የነበሩ ነዋሪዎች ማህበራዊ ችግራቸውን ታሳቢ በማድረግ የቤት እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደረገ

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከህጋዊ የልማት ተነሽዎች ጋር በጥገኝነት ሲኖሩ ለነበሩ ነዋሪዎች ማህበራዊ ችግራቸውን ታሳቢ በማድረግ የቤት እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደረገ።

በዛሬው እለት በክፍለ ከተማው የአዲስ አበባ ት/ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ እና የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ቅድስት ወ/ጊዮርጊስ በተገኙበት ለተጠቃሚዎቹ እጣ የማውጣት ስነ-ስርዓት ተካሂዷል።

በመርሃ -ግብሩ የቤት እድለኛ የሆኑ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር በቀጠና 1 ከልማት ተነሽዎች ጋር በጥገኝነት ሲኖሩ የነበሩ 28 ያህል አባወራዎች የቤት እድል ተጠቃሚ በመሆን በእጣ እንዲካተቱ ተደርገዋል ።

የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ቅድስት በመርሃ ግብሩ እንዳሉት የከተማ አስተዳደሩ ለህጋዊ የልማት ተነሺዎች ምትክ የሰጠ በመሆኑ በጥገኝነት ሲኖሩ የነበሩትን የቤት እድል ተጠቃሚ የማድረግ ግዴታ እንደሌለበት ጠቅሰዋል

ሆኖም ግን የነዚህን ነዋሪዎች የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ለከንቲባዋ እንዲደርስ በማድረግ የነዋሪዎችን አቅምና ማህበራዊ ችግር ከግምት በማስገባት የቤት እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርግዋል ብለዋል

ይህ ተግባር የፓርቲውን ሰው ተኮር እሳቤና ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለእያንዳንዱ ቤተሰብ ህይወት የሚሰጡ ልዩ ትኩረትና ሰብዓዊ ርህራሄ ማሳያ ነው ብለዋል።

የቤት እድል ተጠቃሚዎች በበኩላቸው በተሰጣቸው እድል መደሰታቸውን በመግለፅ ለከተማ አስተዳደሩና ለከንቲባ አዳነች ምስጋና አቅርበዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.