አብሮነት ለሁለንተናዊ ብልፅግና!!

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

አብሮነት ለሁለንተናዊ ብልፅግና!!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ዶ/ር ዓለሙ ስሜ የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ ልደታ ክፍለ ከተማ በሚገኘው የተስፋ ብርሀን የምገባ ማዕከል ማዕድ አጋሩ!

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የትራንስፖርትና ሎጅስቲክ ሚኒስትሩ ዶ/ር ዓለሙ ስሜ በልደታ ክፍለ ከተማ በሚገኘው በተስፋ ብርሀን የምገባ ማዕከል በመገኘት ማዕድ አጋርተዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደገለፁት፤አንድነት ወንድማማችነትና አብሮነት የሚጠናከረው በመደጋገፍ ነው፡፡

በበዓላት ወቅት የሚታዩ አብሮነቶች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸውም ተናግረዋል፡፡

የትራንስፖርትና ሎጅስቲክ ሚኒስትሩ ዶ/ር ዓለሙ ስሜ በበኩላቸው “ባለፉት 5 ዓመታት የመተሳሰብ የመረዳዳትና የመጠያየቅ ባህላችን ተጠናክሯል፥አብሮነትና ወንድማማችነት የበለጠ መዳበር ችሏል” ብለዋል።

“በዓሉን ድጋፍ ከሚሹ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ማሳለፍ መቻላችን እድለኝነት ነው” ያሉት ሚኒስትሩ በበዓሉ አቅም ያላቸው ዜጎች አቅም የሌላቸውን ማዕድ በማጋራት እንዲያሳልፋም ጥሪ አቅርበዋል።

“መደጋገፍ መረዳዳትና መጠያየቅ የእኛ ኢትዮጲያዊያን እሴት ነው” ያሉት የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሰዒድ ዓሊ፤ እነዚህን እሴቶቻችንን የበለጠ በማጠናከር ወንድማማችነትና ህብረትን ማጎልበት ይኖርብናል ማለታቸውን ከክፍለ ከተማው ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.