ባለፈው አመት ነሐሴ ከዳንጎቴ ግሩፕ ጋር በመሆን በአመት 3 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ዩሪያ ማዳበሪያ የማምረት አቅም ያለው ፋብሪካ ለማቋቋም ትልቅ የባለድርሻ ስምምነት አድርገን ነበር። በያዝነው አመት ጥቅምት ወር ደግሞ የፕሮጀክቱን ግንባታ በይፋ ጀምረናል።
ባለፈው አመት ነሐሴ ከዳንጎቴ ግሩፕ ጋር በመሆን በአመት 3 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ዩሪያ ማዳበሪያ የማምረት አቅም ያለው ፋብሪካ ለማቋቋም ትልቅ የባለድርሻ ስምምነት አድርገን ነበር። በያዝነው አመት ጥቅምት ወር ደግሞ የፕሮጀክቱን ግንባታ በይፋ ጀምረናል። ይኽ ሥራ ከመሠረተ ልማት ግንባታም በላይ ነው። በኢትዮጵያ የግብርና ትራንስፎርሜሽን፣ የምግብ ሉዓላዊነት፣ የኢንደስትሪ እድገት እና በኢኮኖሚ ራስ የመቻል ጥረት ውስጥ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያለው ኢንቬስትመንት ነው። የማዳበሪያ ፋብሪካው በሚጠናቀቅበት ወቅት የሀገር ውስጥ የማምረት አቅምን ያጎለብታል፣ ከውጭ በሚገባ ማዳበሪያ ላይ ያለውን ጥገኝነት ይቀንሳል፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አርሶአደሮቻችንን ይደግፋል። ለኢንቨስትመንት እና የሥራ ዕድል ፈጠራም አዳዲስ እድሎችን ይከፍታል።
ዛሬ ማለዳ ከአሊኮ ዳንጎቴ ጋር በመሆን በጎዴ ተገኝቼ ሥራው የደረሰበትን ደረጃ ለመገምገም የፕሮጀክት ስፍራውን ጎብኝቻለሁ። በመላው የፕሮጀክቱ ስፍራ የሚታየው የሥራ ሂደቱ ፍጥነት አበረታች ነው። ይኽን ግዙፍ እና እጅግ ጠቃሚ ሀገራዊ ፕሮጀክት ለመፈፀም ያለውን ቁርጠኝነት እና ትብብር በሚያንፀባርቅ ሁኔታ በተለያዩ የፕሮጀክቱ ክፍሎች ያሉት ግንባታዎች በእቅዳችን መሠረት እየተጓዙ ይገኛሉ።
Last August, in partnership with the Dangote Group, we made significant progress by signing a landmark shareholders’ agreement for a fertilizer plant with a planned annual production capacity of 3 million metric tons of urea. In October 2025, we officially launched construction of the project.
This initiative represents far more than infrastructure. It is a strategic investment in Ethiopia’s agricultural transformation, food security, industrial growth, and economic self-reliance. Once completed, the fertilizer plant will play a vital role in strengthening local production capacity, reducing dependence on imports, supporting millions of farmers, and creating new opportunities for jobs and investment.
This morning, together with Aliko Dangote, I visited the project site in Gode to assess the progress achieved so far. I am encouraged by the steady momentum across the project area. Construction activities are advancing as planned across multiple sections of the site, reflecting the strong commitment and collaboration driving this important national project forward.
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.