ከገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ በተጨማሪ የአካባቢውን ገጽታ እና የነዋሪዎችን ሕይወት ሙሉ በሙሉ ከስር መሠረቱ ለመለወጥ ምን አይነት ግንባታዎች ተከናወኑ?
በአዲስ አበባ የመጀመሪያው እና ትልቁ ባለ 325 ሜትር ርዝመትና 60 ሜትር ስፉት ዘመናዊ ድልድይ፣
21 ነጥብ 73 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው (ቃሊቲ ቀለበት -ቱሉዲምቱ
እና ቃሊቲ ቀለበት - ቂሊንጦ አደባባይ) የኢትዮጵያ የንግድ ኮሪደርን ያሳለጠ እና ቀጥታ ከአየር መንገድ ካርጎ የሚያገናኝ ዘመናዊ የመንገድ መሠረተ ልማት፣
የከተማዋን የመኖርያ ቤት አቅርቦት ችግር ለማቃለል አዲስ ከተማን የመገንባት ያህል የሆነ 60 ሺህ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ፣
ከካዛንቺስ አካባቢ ለልማት ለተነሱ ነዋሪዎች የተገነባው ምቹና የተቀናጀ ዘመናዊ የመኖሪያ መንደር
የኅብረተሰቡን ጤና በላቀ ደረጃ ለመጠበቅ በከተማዋ በትልቅነቱ ቀዳሚ የሆነው የገላን ትሯማ ሆስፒታል:
በአካባቢው ለዚሁ ልማት ለእርሻ ሲጠቀሙበት የነበረውን መሬት ለለቀቁል አርሶ አደሮች የተቀናጀ ዘመናዊ የግብርና ልቀት ማዕከል :
መንፈስን የሚያድሱ ሰፋፊ አረንጓዴ ስፍራዎችና ፓርኮች፣
የስፖርት ማዘውተሪያዎችና የልጆች መጫወቻዎች፣
ለእናቶች ሰፊ የስራ ዕድል የሚፈጥር የእንጀራ ፉብሪካ ግንባታና የመሳሰሉት የብልፅግና አሻራዎች ተገንብተዋል
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.