ዛሬ ከሴከተር፣ ከክፍለ ከተማ እና ከወረዳ አመራ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ ከሴከተር፣ ከክፍለ ከተማ እና ከወረዳ አመራሮች ጋር የአገልግሎት አሰጣጥን፣ የኑሮ ውድነት ጫናን ለመቀነስ፣ ገበያን ለማረጋጋት እና ለማረቅ እየሰራን ያለነውን ስራ ገምግመናል።

 

በመደበኛው አሰራርም ሆነ በመሶብ ዲጂታል የአንድ ማዕከል የአገልግሎት አሰጣጥ ባቀድነው መሰረት እየተሻሻለ መሆኑን እና የኑሮ ውድነት ጫናን ለመቀነስ፣ ገበያን ለማረጋጋት እና ለማረቅ እየሰራን ያለነውም ስራ በአብዛኛው ውጤታማ ሲሆን፤  በነዳጅ ምክንያት ከፍ ያሉ የአንዳድ ሸቀጦች ዋጋዎች አሁንም በተሟላ ሁኔታ እንዳልወረዱ ተረድተናል።
በመሆኑም አንዳንድ የማስተካከያ እርምጃዎችን መውሰዳችንን አጠናክረን እንቀጥላለን።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.