ዛሬ በአደስ ከተማ ክፍለ ከተማ ገብስ ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው ቁጥር 3 የበጎነት መንደር የተገነባውን 44 የመኖሪያ ቤቶች እና ሱቆች ያሉት ባለ አምስት ወለል ህንጻ ለተጠቃሚዎች አስተላልፈናል።
ገብስ ተራ ቀደም ብሎ እጅግ የተጎሳቆለ እና ለመኖር ምቹ ያልሆነና ባረጁ እና በደቀቁ ቤቶች የተሞላ፤ በተደጋጋሚ በእሳት አደጋ የሚጠቃ ፣ ለአቅመ ደካሞች እናቶች የማብሰያና የመጸዳጃ አገልግሎት አስቸጋሪ የነበረበት መንደር ነበር።
በዚህ መንደር የዛሬውን ጨምሮ በአጠቃላይ 377 የመኖሪያ ቤቶች ያላቸው 5 ህንጻዎችን መገንባት የቻልን ሲሆን ነዋሪዎቻችንም ከዛ አስከፊ አኗኗር ተላቀው ክብራቸውን በሚመጥን ፅዱ፥ ዘመናዊ አኗኗር የሚፈጥር፥ ልጆች ቦርቀዉ የሚጫወቱበት እና ደረጃውን በጠበቀ መኖሪያ መንደር እንዲኖሩ በማድረጋችን በጣም ደስ ብሎናል ።
ይህንን የበጎነት መንደር ግንባታ ላይ በክትትል እና ድጋፍ አስተዋጽኦ ያደረጉ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮቻችን ከምንም በላይ ልበ ቀና ባለሀብቶች በገንዘባቸው ላደረጉት ድጋፍ በነዋሪዎቹ ስም ከልብ አመሰግናለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.