ታዋቂው ቲክቶከር ዲላን ፔጅ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኘ
ዲላን ፔጅ የዲጂታል ጋዜጠኛ እና የማህበራዊ ሚዲያ ይዘት ፈጣሪ በኢንስቲትዩቱ በመገኘት የተቋሙን ስራዎች ተመልክቷል፡፡
ዲላን ፔጅ ጉብኝቱን አስመልክቶ በሰጠዉ አስተያየት “ይህ ጉብኝት በዓለማቀፍ ደረጃ ስለ አፍሪካ ያለውን የተዛባ አመለካከት የሚቀይር ነው። ይህን በቴክኖሎጂ የተቃኘ ቦታ ሳየዉ ተደምሜያለሁ። በጣም ያማረና አስደናቂ ቦታ ነዉ። አፍሪካ ተቀይራለች አዲሱን ገፅታዋን ለዓለም የሚያሳይ ቦታ ሆኖ አጊኝቼዋለሁ። ባየሁት ነገር ደስተኛ ነኝ።” ሲል መግለጹን ከኢንስቲትዩቱ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡
ዲላን በተለይም ለወጣቶች በሚመች መልኩ በፈጣን አቀራረብ፣ አጭር፣ ሳቢ እና ለመረዳት ቀላል የሆኑ ዓለማቀፍ ዜናዎችን እና ወቅታዊ ሁኔታዎችን በማቅረብ ይታወቃል።
በቲክቶክ ከ19 ሚሊዮን በላይ ተከታይ ያለው ዲላን፥ በራሱ ልዩ የአቀራረብ ዘይቤ ዓለማቀፍ ተከታዮችን ማፍራት የቻለ ሲሆን፤ በተለይም ወጣቱ ትውልድ ዜናን የሚቀበልበትን መንገድ በመቅረጽ ረገድ ትልቅ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።
AMN
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.