"ከተማ አስተዳደሩ የትንሳኤ በዓልን በደስታ እን...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

"ከተማ አስተዳደሩ የትንሳኤ በዓልን በደስታ እንድናሳልፍ አድርጎናል"-በማዕድ ማጋራት የታደሙ የህብረተሰብ ክፍሎች

“ከተማ አስተዳደሩ የትንሳኤ በአልን ተደስተን እንድናሳልፍ አድርጎናል” ሲሉ በለሚኩራ ክፍለ ከተማ የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ በተከናወነው የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር ላይ የታደሙ የህብረተሰብ ክፍሎች ተናገሩ፡፡

ከአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ጋር ቆይታ ያደረጉ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደገለፁት ባለፉት ዘመናት በዓልን ያለ አስታዋሽ ተቸግረው ያሳልፉ እንደነበር አስታውሰው አሁን ግን በክፍለ ከተማውም ሆነ በከተማ ደረጃ አስታዋሽ ያጣነውን በማስታወስ በተለያዩ የምገባ ማዕከላት እና በልዩ ልዩ መርሃ ግብሮች እየደገፈን ነው፡፡ 

“በተለይም የትንሳኤ በዓልን የምንበላውና የምንጠጣው ሳናጣ እና አብሮን የሚያሳልፍ ሳይናፍቀን ደስ ብሎን እንድናሳልፍ አድርጎናል” ብለዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ በክብር እንግድነት የተገኙት የከተማዋ የብልፅግና ፓርቲ አደረጃጄት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ይመር ከበደ በበኩላቸው እንደከተማ በርካታ አስታዋሽ ያጡ ዜጎችን በማስታወስ መረዳዳት፣ መደጋገፍ፣ አብሮነትና አንድነትን ከፍ የሚያደርጉ ጠንካራ ሀገራዊ እሴቶቻችን እንዲጎለብቱ ሰፋፊ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ታረቀኝ ገመቹ በበኩላቸው፤ በክፍለ ከተማው በሚገኙ ሁለት የምገባ ማዕከላት በርካታ ዜጎች ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልፀው የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግም ክፍለከተማው በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ዜጎች በዓልን ተደስተው እንዲያሳልፉ የተለያዩ ድጋፎች መደረጋቸውን ተናግረዋል፡፡ ይህ የመደጋገፍ ባህል ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ከክፍለ ከተማው ባለሀብቶችና ነዋሪዎች ጋር የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ ስለመሆኑም ተናግረዋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.