አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ እና አበባ የማድረግ ስራችን አካል በሆነው የነገዋ የሴቶች የተሀድሶ እና የክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል ሰልጣኞች ጋር የትንሳኤ በዓልን አብረን አክብረናል::
የትንሳኤ በዓልን አብረን ለማሳለፍ የጋበዝናቸው እንግዶች በማዕከሉ በስልጠና ላይ ለሚገኙ ለሁሉም እህቶቻችን የስራ እድል በመፍጠር አብረውን ለመስራት ቃል የገቡ ሲሆን እነዚህን ልበ ቀና ባለሃብቶች በሰልጣኝ ሴት እህቶቻችን ስም ላመሰግናቸው እወዳለሁ::
አዲስ አበባችንን ማህበራዊ ፍትህ የነገሰባት የሁሉም ከተማ የማድረግ ስራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.