ኢትዮጵያ ከፈረንጆቹ 2024 እስከ 2029 ባሉት...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ኢትዮጵያ ከፈረንጆቹ 2024 እስከ 2029 ባሉት አምስት ዓመታት በዓለም ላይ በፍጥነት በማደግ ላይ ያሉ አዳዲስ ገበያዎች ከሚኖራቸው 10 ሀገራት መካከል 5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

ትላልቅና እያደጉ ያሉ ገበያዎች በሕዝብ ቁጥር ዕድገትና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በሚሄድ የሸማቾች ፍላጎት ምክንያት ወደፊት ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ዕድገት ላይ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወቱ ይገመታል።

ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ አገራት በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ውስጥ ኢኮኖሚያቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ በአማካይ በእጥፍ እንደሚያድግ ይገምታል። 

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) ባወጣው የዓለም ኢኮኖሚክ አውትሉክ ትንበያ መሠረት ከ2024 እስከ 2029 ድረስ በከፍተኛ ፍጥነት ዕድገት በማሳየት ላይ ያሉ ገበያዎችን ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሰረት፡- ጉያና (19.8 በመቶ)፣ ሞዛምቢክ (7.9)፣ ሩዋንዳ (7.2)፣ ባንግላዴሽ (6.8 )፣ ኢትዮጵያ (6.7)፣ ኒጀር (6.7)፣ ዩጋንዳ (6.6)፣ ሕንድ (6.5)፣ ቬትናም (6.4) እንዲሁም ሴኔጋል (6.3) በመቶ ዕድገት ያሳያሉ ተብሎ እንደሚገመት መረጃው ያሳያል። 

#Addisababa   

#Ethiopia


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.