ድምጻችንን በመስጠት የነገ ተስፋችንን እውን ለ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ድምጻችንን በመስጠት የነገ ተስፋችንን እውን ለማድረግ ተዘጋጅተናል - የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች

አስተያየታቸውን ለኤ ኤም ኤን ዲጂታል የገለጹት የከተማዋ ወጣቶች "ድምፄ ዋጋ አለው!" በሚል ጽኑ እምነት የምርጫ ካርዳቸውን ከመውሰድ ባለፈ ተወዳዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሲያደርጓቸው የነበሩትን የፖሊሲ ክርክሮች እና ምክክሮችን በጥሞና ሲከታተሉ መቆየታቸውን አስታውሰዋል፡፡ 

ወጣቶቹ ፤ ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ምዕራፍ ሊያሻግር፣ እንዲሁም ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጥያቄዎቻቸውን ሊፈታ የሚችል የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ መወሰናቸውንም አብራርተዋል።

በተለይም ለመጀመሪያ ጊዜ ድምፃቸውን የሚሰጡ ወጣቶች ቀኑን በከፍተኛ ጉጉት እየጠበቁት መሆኑን በመግለጽ ሁሉም ወጣት በወሰደው ካርድ፣ ድምጹን በመስጠት ሀገርን የተሻለች፣ ዲሞክራሲያዊት እና የበለጸገች ለማድረግ አሻራውን ሊያሳርፍ ይገባልም ብለዋል፡፡

AMN


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.