አዲስ አበባ እየመረጠች ነዉ!!!

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

አዲስ አበባ እየመረጠች ነዉ!!!

"የመምረጥ መብቱን እያስከበረ ያለ እና ዋናዉ የስልጣን ምንጭ የህዝብ ድምፅ ብቻ እና ብቻ መሆኑን ያስመሰከረ ታላቅና ጨዋ ህዝብ ነዉ፡፡"

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በመዲናዋ ነፃ፤ግልፅ፤ዲሞክራሲያዊ እና ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ምርጫ እየተካሄደ መሆኑን የጠቀሱት ከንቲባ አዳነች አቤቤ የከተማችን ነዋሪ ከምርጫ ጣቢያዎች በር መከፈት አስቀድሞ ማልዶ በመገኘት ያለአንዳች ተፅእኖ የመምረጥ መብቱን እያስከበረ ያለ እና ዋናዉ የስልጣን ምንጭ የህዝብ ድምፅ ብቻ እና ብቻ መሆኑን ያስመሰከረ ታላቅና ጨዋ ህዝብ ነዉ ብለዋል፡፡

ይህም ለሃገራችን ዘላቂ ልማት እና ሰላም መሳካት ወሳኝ ምእራፍ በመሆኑ በትዕግስት እና በፅናት የተጀመረዉ ድምፅ አሰጣጥ እስከ መጨረሻዉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ድምፅ በሰጡበት የምርጫ ጣቢያ መልእክታቸዉን አስተላልፈዋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.