አዲስ አበባን እንደስሟ ውብ እና አበባ ለማድረግ እየሰራናቸው ካሉ ስራዎቻችን መካከል አንዱ በሆነው የኮሪደር ልማት ስራ ላይ ከተሰማሩ ሰራተኞች፣ ኮንትራክተሮች፣ አማካሪዎች እንዲሁም አመራሮች ጋር በዓድዋ ድል መታሰቢያ ተገኝተን እንኳን ለትንሣኤ በአል አደረሳችሁ ብለን አበረታተናቸዋል።
በዚህ የኮሪደር ልማት በተለወጠው አዲሱ የስራ ባሕላችን መሠረት፣ በዓላትን ጨምሮ 24/7 በሚመሩ፣ በሚያስተባብሩ እንዲሁም በሚሰሩ ትጉህ ሰራተኞች በሀገራችን አይተነው የማናውቀውን የስራ ቅልጥፍና፣ ጥራትና ውጤት ተመልክተናል።
መንገዶቻችን ለእግረኛ፣ ለሞተር አልባ ተሽከርካሪ እና ለብዙሀን ትራንስፖርት አገልግሎት የተመቹ እንዲሆኑ፤ የህዝብ የጋራ መገልገያ መሰረተ ልማቶችን ለማሟላት፤ ጽዱ፣ ለመኖር ምቹ፣ አረንጓዴ እና ውብ አዲስ አበባን ለመገንባት በፕላናችን መሠረት ዲዛይን ከማዘጋጀት እስከ ግንባታ ድረስ ያለውን ስራ በላቀ የኃላፊነት ስሜት፣ የሙያ ብቃትና ትጋት እየመራችሁና እያስተባበራችሁ ያላችሁ አመራሮች፣ መሀንዲሶች፣ ባለሙያዎች፣ ኮንትራክተሮች፣ አማካሪዎች እንዲሁም ለስራ የተመቻቸ ዓውድ ለመፍጠር በንቃት የተሳተፋችሁ የጸጥታ አካላት እኛ ብቻ ሳንሆን የከተማችሁ ነዋሪዎችም ያመሰግኗቹኋል።
ተባብረን የማይገፋ የመሰለውን ተግዳሮት እየተሻገርን ከተማችንን የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ በላቀ ትጋት ማገልገላችንን እንቀጥላለን!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.