ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው
የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች፣ ትዕግስታችሁና ጽናታችሁ እጅግ በጣም የሚደነቅ ነው።
በዘንድሮው ምርጫ ኢትዮጵያችንን ለማጽናት፣ ዘላቂ ሰላምንም ለማረጋገጥ እና የሀገረ መንግስት ግንባታችንን ለማጠናከር ያላችሁን ቁርጠኝነት ዳግም አሳይታችኋል።
ለረጅም ሰዓት እስካሁን ድረስ ተሰልፋችሁ ያላችሁ፣ ሕፃን ልጃችሁን በጀርባችሁ ያዘላችሁ እመጫቶች፣ ነፍሰ ጡር እናቶች፣ የአካል ጉዳተኞች፣ አዛውንቶች፣ ጎልማሶች እና ወጣቶች፤ ምዝገባው ዲጂታል የነበረ እና በወረቀት ፕሪንት የተደረገ በመሆኑ የምርጫ ቦርድ አስፈፃሚዎች የስም ፍለጋ ጊዜ መውሰዱ የፍጥነት ላይ ችግር በማጋጠሙ ይቅርታ ጠይቋል ።
በመሆኑም ይህንን በመረዳት እንደጀመራችሁት በጽናት ይበጀኛል ያላችሁትን ለመምረጥ በትግስት ምርጫችሁን እንድታከናውኑ እጠይቃለሁ።
#ኢትዮጵያእየመረጠችነው #ኢትዮጵያ #ዲሞክራሲ #የሕዝብሉዓላዊነት
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.