የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ሩጫ እየተካሄደ ነው
19ኛው የኢትዮጵያ የግማሽ ማራቶን ውድድር በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
መነሻ እና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገው ውድድሩ በወንዶች 455 እና በሴቶች 183 በድምሩ 638 አትሌቶች እየተሳተፉበት እንደሚገኝ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል።
በዴንማርክ ኮፐንሀገን ለሚካሄደው የግማሽ ማራቶን ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶች በውድድሩ እንደሚመረጡ ተገልጿል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.