ቃል በተግባር በከተማችን ተጠናክሮ ቀጥሏል---

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ቃል በተግባር በከተማችን ተጠናክሮ ቀጥሏል---


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጅታል የመንግስት አገልግሎት የካ ማዕከልን መርቀው አስጀመሩ።

በም/ከንቲባው የተመረቀው የየካ ማዕከል በከተማችን 9ኛው መሶብ ዲጅታል የመንግስት አገልግሎት ነው።

መሶብ በከተማ አስተዳደሩ የአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ያሉ የህዝቡን ቅሬታዎችን እየፈታ መሆኑንም አቶ ጃንጥራር አባይ ተናግረዋል።

በዚህ ዓመት ቀደም ሲልና አሁን ላይ ወደ ስራ በገቡ የመሶብ ማዕከላት የተገልጋዮች እርካታን 99 በመቶ ማድረስ ተችሏል።

ይህን የነዋሪዎችን የአገልግሎት እንግልት ለማስቀረት ከምርጫ ማግስትም አዳዲስ  የመሶብ ዲጅታል ማዕከላትን ወደ ስራ የማስገባት ጥረታችንን አጠናክረን በመቀጠል 9ኛው የየካ ማዕከል ላይ ደርሰናል።

በቀጣይ ጥቂት ቀናት ደግሞ ግንባታቸው የተጠናቀቁትን የአቃቂና የለሚ ኩራ ማዕከላትን ወደ ስራ የምናስገባ ይሆናል።

ተጨማሪ ስራ በመስራት የህዝባችንን እርካታ እንዲጨምር እናደርጋለን ሲሉም አቶ ጃንጥራር ተናግረዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.