“ከተማ አስተዳደሩ ለነዋሪዎች አካታች፣ ተደራሽና...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

“ከተማ አስተዳደሩ ለነዋሪዎች አካታች፣ ተደራሽና ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት አየሰራ ነው!”

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ  ኃላፊ ጀማሉ ጀምበር (ዶ/ር)

ከተማ አስተዳደሩ ለነዋሪዎች አካታች፣ ተደራሽና ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት አየተሰራ ነው ሲሉ ዶር ጀማሉ ጀንበር ገለፁ።

አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አላስፈላጊ የቢሮክራሲ አሰራርን ያስቀረና ተጠያቂነትን ያሰፈነ ነውም ብለዋል።

በዛሬው ዕለት ለአገልግሎት የበቃው የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጅታል የመንግስት አገልግሎት የየካ ማዕከል 96 ተገልጋዮችን በአንድ ጊዜ ማስተናገድ የሚያስችል መስኮትና ሌሎች መሰረተ ልማቶች የተሟሉለት መሆኑን አስረድተዋል።

ማዕከሉ የ22 ተቋማትን 114 አገልግሎት መስጠት ያስችላል። በቀጣይ ተጨማሪ አገልግሎቶች እንደሚጀምሩ አስታውቀዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.