ዛሬ በምርጫ ሥራዎቻችን አፈጻፀምና የድህረ ምርጫ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ በምርጫ ሥራዎቻችን አፈጻፀምና የድህረ ምርጫ ሥራዎቻችን በውጤታማነት በመከወን ከመላው የከተማችን አመራሮች ጋር ገምግመናል ።ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ዛሬ በምርጫ ሥራዎቻችን አፈጻፀምና የድህረ ምርጫ ሥራዎቻችን በውጤታማነት በመከወን የያዝናቸውን ግቦች በተሟላ መልኩ ከማሳካት አንፃር  የተገኙ ዉጤቶችን ከመላው የከተማችን አመራሮች ጋር ገምግመናል ።

7ኛውን ጠቅላላ ሃገራዊ ምርጫ በስኬት እንዳይጠናቀቅ ለማደናቀፍ በውጭም በውስጥም በጋራ በማበር  በሚደያ ዘመቻዎች እና በተለያዩ ቅስቀሳዎች  ሰላም የማደፍረስ   ዝግጅቶችና ትንኮሳዎች  ተደርገው ሳይሳካላቸው  በኢትዮዽያ ታሪክ ትልቅ እድገት የታየበት  ዴሞክራስያዊ፥ ሰላማዊና ተዓማኒ ምርጫ በማካሄድ ኢትዮዽያዊን በፅናት  አዲስ ታሪክ  ፅፈዉ ኢትዮጲያ መርጣለች፥ ኢትዮጵያ አሸንፋለች።

እንደሃገር ያሳካነው እጅግ ውጤታማ እና ታሪካዊ ምርጫ  የህዝባችን ፣የአመራራችን፣  የአባሎቻችን  ፣የደጋፊዎቻችን፣የሲቭክ ማህበራት ፣  የሚድያዎቻችን፣ ተፎካካሪ  የፓለቲካ ፓርቲዎች እንዲሁም በገለልተኝነትና በከፍተኛ ዲሲፕሊን ትልቅ ሃገራዊ ሃላፊነታቸዉን  የተወጡት  የፀጥታ አካላትና የምርጫ ቦርድ  በጥቅሉ ሁሉም ባለድርሻ አካል እንደ ሀገር  ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ያላንን  ቁርጠኝነትና በጋራ ያሳካነው  ግብ  መሆኑን  ተግባብተናል ። ለዚህም ሁሉንም ባለድርሻ አካላት እናመሰግናለን።

  የድህረ ምርጫ ስራዎቻችን በውጤታማነት በመፈፀም  ይህንን ፅኑ ህዝብ  ለመካስ ያስቀመጥናቸዉን  ግቦች በተሟላ መልኩ ለማሳካት  ከመላው አመራራችን ጋር ተግባብተናል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.