በሽታን ከመከላከል ኣክሞ እስከማዳን ዓቅም የገነ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በሽታን ከመከላከል ኣክሞ እስከማዳን ዓቅም የገነባች፣ የጤና ቱሪዝም ማዕከል ውቢቷ መዲናችን አዲስ አበባ!

 

ባለፉት ጥቂት ዓመታት የተገነቡ፣ የታደሱ የጤና ተቋማት የአዲስ አበባን በጤና መሠረተ-ልማት ልዕልና ማሳየት የቻሉ ከመሆናቸው በተጨማሪ፣ የጤና ቱሪዝምን በማሳደግ የዘርፉን የአገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት ያላቁ ዘመን ተሸጋሪ፣ ትውልድ አኩሪ ስኬታማ ሥራዎች ናቸው፡፡

በመዲናችን አዲስ አበባ፣ ለዜጎች ጤና ቅድሚያ በመስጠት ከተማዋ ንፁህ፣ ምቹ እና ለመኖር ምቹ ከማድረግ ጎን-ለጎን ለእግር ጉዞ፣ ለብስክሌት እና መሰል ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች የተመቹ ስፍራዎች፣ ለጤና ጠንቅ የነበሩ የተበከሉ ወንዞች አክሞ ለአፍንጫም ለአይንም ውብ እንድትሆን በትኩረት በመስራት፣ በሽታን አስቀድሞ ለመከላከል እንዲያስችል ተደርጎ ተሰርቷል፡፡
 
ከመከላከል ባለፈ፣ የዜጎችን ጤና ለመታደግ፣ አክሞ ለማዳን የሚያስችሉ እንደነ ላፍቶ ሆስፒታል በምስራቅ አፍሪካ የመጀመርያ የሆኑ የህክምና ግብኣት የተሟላላቸው  አዳዲስ ዘመናዊ ሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎችን በመገንባት፣ እንዲሁም ነባሮቹን እንደነ ዘውዲቱ ሆስፒታል እና ሌሎች ከዘመሙበት ቀና አድርጎ ዳግም በማነፅ፣  በሰው ሃይል እና በዘመናዊ ቁሳቁስ በማደራጀት ቀን-ከሌሊት እየሰራ ይገኛል፡፡ ከዚሁም ባለፈ፣ ዜጎች የተሸለ ህክምና ለማግኝት ወደ ሌሎች ሀገራት የሚያደርጉት ጉዞ ማስቀረት አስችለዋል፡፡ በአንፃሩ በከባቢው የሚገኙ ሃገራት ለተሸለ ህክምና የሚመጡባት የጤና ቱሪዝም ማዕከል በመሆን ትገኛለች፡፡ 

አዲስ አበባ የሁለንተናዊ ዕድገት ካባ የተጎናፀፈች ከተማ!


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.