አፍሪካዊት የብልፅግና ተምሳሌት የሆነች ሀገር የመገንባት ራዕይን ከግብ ለማድረስ ሁለንተናዊ የልማት ዕቅዶቻችን ሳይቆራረጡ ተግባራዊ ማድረግ ይገባል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ፡፡ የፌደራል ተቋማት የሱፐርቪዥን ማጠቃለያ ሪፖርት ግምገማ ዛሬ ተካሂዷል፡፡
በመድረኩ ከመስክ ምልከታ የተገኙ ሪፖርቶችን ጨምሮ የተቋማት አፈፃፀም ጠለቅ ባለ እና በተደራጀ መልኩ ሪፖርት ቀርቧል፡፡
ዕቅዶች መሬት ላይ ወርደው ሲተገበሩ ምን ውጤት አመጡ፣ በትግበራ ሂደቱ ያጋጠሙ ችግሮች ምን ይመስላሉ፣ እንዲሁም በቀጣይ በመረጃ እና በትንተና የተደገፈ አካሄድ እንዴት መፍጠር እንደሚቻል በመድረኩ ተነስቷል፡፡
በሱፐርቪዥኑ ሪፖርት በመልካም ጅማሮ የታየው ዋንኛው ጉዳይ ዲጅታላይዜሽን ነው፡፡ የዲጂታል አገልግሎት ግልፅ፣ ተዓማኒነት ያለው፣ ፈጣን የአገልግሎት ስርዓት ደረጃ በደረጃ በመዘርጋት የህዝቡን ህይወት ለማሻሻል መሰረታዊ ተግባር ነው፡፡ ስለዚህም የዲጂታል ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ቁርጠኝነት ወሳኝ እንደሆነ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገልፀዋል፡፡ በተጨማሪም ይህን የሱፐርቪዥን ስራ በቀጣይ አጠናክሮ መስራት እንደሚገባ የተናገሩ ሲሆን ለዚህ ደግሞ ዲጂታላይዜሽን አይነተኛ መፍትሄ ነው ሲሉ አሳስበዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.