የአዲስ አበባን ገፅታ የቀየረውና ለኑሮ ምቹ ያደ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአዲስ አበባን ገፅታ የቀየረውና ለኑሮ ምቹ ያደረገው አረንጓዴ አሻራ

ተፈጥሮ ንጹህ አየርን፣ ዝናብንና ለምለም መሬትን በመለገስ የሰውን ልጅ ህልው ስትደግፍ፣ ሰው ደግሞ እሷን በመንከባከብና በመጠበቅ ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል።

ይህንኑ የተፈጥሮ ሚዛን ለመጠበቅ በ2011 ዓ.ም የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ አገራዊ ንቅናቄ፤ በማኅበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊና በአካባቢያዊ ገጽታ ላይ ዘርፈ-ብዙ ፋይዳዎችን እያስገኘ ይገኛል። 

የአዲስ አበባ ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ለኤ ኤም ኤን ዲጂታል እንደገለጸው፤ ባለፉት ሰባት ዓመታት በመዲናዋ 90 ሚሊዮን ችግኞች የተተከሉ ሲሆን፣ ከተተከሉት ውስጥ 86 ነጥብ 82 በመቶ የሚሆኑት ፅድቀዋል። 

ከተተከሉት መካከልም ለምግብ የሚሆኑ የፍራፍሬ ዛፎች እንዲሁም ለባህላዊና ዘመናዊ ሕክምና የሚያገለግሉ ዕፅዋት እንደሚገኙበት ዳይሬክቶሬቱ አክሎ ገልጿል።

ይህ ታላቅ ንቅናቄ የከተማዋን ሥነ-ምህዳር ከማደስ ባለፈ፣ የአካባቢ ብክለትን በመከላከልና የአየር ንብረት መዛባትን በመቋቋም ረገድ የጎላ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።

ከተማዋን ውብና ለኑሮ ተስማሚ ከማድረግ ባሻገር፣ ለነዋሪዎች ምቹ የሆኑ በርካታ አረንጓዴ የመዝናኛ ቦታዎችን ለመፍጠርም አስችሏል። 

በተጨማሪም ለአካባቢው ዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን፥ ለሀገሪቱ የዲፕሎማሲ ገፅታ ግንባታም ትልቅ አዎንታዊ አስተዋጽኦ አበርክቷል።

ይህንኑ ስኬት በላቀ ደረጃ ለማስቀጠል፣ በዘንድሮው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር 5 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል በከተማዋ ሰፊ የቅድመ-ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ ናቸው። 

የዘንድሮውን ዕቅድ ስኬታማ ለማድረግ በአሁኑ ወቅት የችግኝ ማፍላትና ማጓጓዝ፣ የጉድጓድ ቁፋሮ፣ ሰፊ የሕዝብ ንቅናቄ መፍጠርና ለዘርፉ ባለሙያዎች ሥልጠና የመስጠት ሥራዎች በተሟላ ሁኔታ መከናወናቸውን ዳይሬክቶሬቱ አስታውቋል።

ይህ ታላቅ አገራዊ ንቅናቄ መዲናዋ ነዋሪዎቿን ባሳተፈ መልኩ አረንጓዴና ለኑሮ ተስማሚ የሆነች ከተማ ለመፍጠር እየተደረገ ያለውን ዘላቂ ጥረት ይበልጥ የሚያጠናክረው መሆኑ ተገልጿል።

AMN


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.