ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞንን ግንባታ በኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት እና በሲሲኢሲሲ መካከል በተደረገ በገዳ የኢኮኖሚ ዞን የሉሜ ነፃ የንግድ ቀጠና ማልማት ስራ የመግባቢያ ስምምነት መርሃግብር አስጀምረዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
በገዳ የኢኮኖሚ ዞን የሉሜ ነፃ የንግድ ቀጠና ማልማት ስራ የመግባቢያ ስምምነት መርሃግብር አስጀምረዋል። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር በንግግራቸው በግብርና የተገኘው ስኬት በኢንደስትሪው ዘርፍ የመድገምን አስፈላጊነት አፅንዖት ሰጥተው ያነሱ ሲሆን ለዚህም የፖሊሲ ድጋፍ ብሎም ለኢኮኖሚ ዞኑ ቀጣይ እንቅስቃሴ ጠንካራ የመሰረተ ልማት ስራ ሊከናወን እንደሚገባ አስምረውበታል።
ከአዲስ አበባ ከተማ በስተምሥራቅ በ65 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው ይህ ተቋም ኤክስፖርትን ለማሳደግ፣ የንግድ እና ሎጂስቲክስ ማዕከል የመመስረት፣ የወጭ ኢንቨስትመንትን የመሳብ፣ የኢንደስትሪ የንግድ ኢንቨስትመንት እና የከተማ ልማት ስራዎችን የማበልፀግ አላማ ያነገበ ነው።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.