የአፍሪካ መሪዎች የትውልድ ግንባታ ስራችንን ጨም...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአፍሪካ መሪዎች የትውልድ ግንባታ ስራችንን ጨምሮ በአዲስ አበባ በተሰሩ ዋና ዋና የልማት ስራዎች ዙሪያ ልምድ ለመካፈል አዲስ አበባ ገብተዋል::

ለልምድ ልውውጡ ከተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት የመጡ የአፍሪካ መሪዎች እና ከተለያዩ አለምአቀፍ ድርጅቶች የመጡ እንግዶችን ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይ ተቀብለው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በማስጎብኘት ላይ የሚገኙ ሲሆን በልምድ ልውውጥ መርሃ ግብሩ ላይ የሃገራችን ክልሎች ምክትል ርዕሳነ መስተዳድሮች እና ሚኒስትሮችም የሚሳተፉ ይሆናል::

ከቆይታ በኃላ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንግዶቹን በጽ/ቤታቸው የሚቀበሏቸው ሲሆን በቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም እና የከተማችን ዋና ዋና የልማት ስራዎች ዙሪያ የፓናል ውይይት የሚከናወን ይሆናል::


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.