አዲስ አበባ ለሕጻናት ደህንነትና ዕድገት ምቹ ም...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

አዲስ አበባ ለሕጻናት ደህንነትና ዕድገት ምቹ ምህዳር እየፈጠረች ነው - አፈጉባኤ ቡዜና አልከድር

አዲስ አበባ ከተማ ለሕጻናት ደህንነት ጥበቃና ለዕድገታቸው ምቹ ምህዳር እየፈጠረች ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈጉባኤ ቡዜና አልከድር ገለጹ፡፡ 

36ኛው የአፍሪካ ሕጻናት ቀን ማጠቃለያ ለህጻናት የምትመች ከተማን የመፍጠር ራዕይ ማሳያ በሆነው አራዳ ፓርክ ተከብሯል፡፡ 

ቀኑ የተከበረው ''ደህንነቱና ንጽህናው የተጠበቀ አካባቢ ለሁሉም ህጻናት'' በሚል መሪ ሀሳብ ሲሆን አከባበሩ ላይ ሕጻናት የተለያዩ ትርዒቶችን አሳይተዋል፡፡ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ ሕጻናትና ታዳጊዎችም በበዓሉ ተሳትፈዋል። 

በአከባበሩ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈጉባኤ ቡዜና አልከድር፤ ከተማዋ ለሕጻናት ምቹ እንድትሆን አስተዳደሩ ትልልቅ ስራዎች መስራቱን ተናግረዋል። 

የነገዋ ጠንካራ ሀገር ግንባታ መሰረት የሆኑት ሕጻናት ላይ ከተማዋ በትኩረት እየሰራች ነው ያሉት አፈጉባኤዋ ከተማዋ ለሕጻናት ደህንነት ጥበቃና ለዕድገታቸው ምቹ ምህዳር እየፈጠረች ነው ብለዋል። 

የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ በበኩላቸው፤ ቀኑ ከወረዳ ጀምሮ የህሕጻናት መብትና ደህንነት ግንዛቤን ባሳደገ መልኩ ሲከበር መቆየቱን ገልጸዋል፡፡ 

AMN


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.